Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ 50 አመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከካናዳ፣ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከቱርክ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጣልያን. | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የዛሬ 50 አመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከካናዳ፣ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከቱርክ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጣልያን... ወዘተ ይበልጣል?

አንዳንድ 'ተቀፅላዎች' ይህን ስክሪንሾት በስፋት ሲያጋሩ እንደነበር ጥቆማዎች ደርሰውኝ ነበር፣ እንዲጣራም የጠየቁ አሉ። ነገሩ እንዲህ ነው፣

መረጃው በ Goldman Sachs የ 2022 ሪፖርት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እ.አ.አ በ 2075 ወይም የዛሬ 50 አመት 6.2 ትሪሊየን ዶላር የማደግ እድል እንዳለው ይጠቁማል። በዚህ መረጃ ላይ ታድያ እነ ከካናዳ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ቱርክ፣ አውስትራሊያ፣ ጣልያን ከኢትዮጵያ በታች የተቀመጡ ሲሆን ቻይና፣ ህንድ እና አሜሪካ ከ 1-3 ያለውን ቦታ ይዘዋል።

እውነታው ግን ወዲህ ነው፣

እንዲህ አይነት የኢኮኖሚ እድገት ትንበያዎች በአብዛኛው የወደፊት የማደግ አቅምን የሚያሳዩ ሲሆን በርካታ አሁናዊ እና የወደፊት እድሎችን እና መሰናክሎችን አያካትትም። በተጨማሪም ይህ አሀዝ በከፍተኛ ደረጃ የሚንተራሰው የህዝብ ብዛት ቁጥር ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት በ2075 አካባቢ 281 ሚልዮን ይገመታል፣ ይህም ለከፍተኛ ምርታማነት እና የኢኮኖሚ እድገት መሰረት የመሆን እድል አለው። ሪፖርቱ የጠቀሰውም ይህን ነው።

ይሁንና ተቀፅላዎቹ ሊያቀርቡት እንደፈለጉት ይህ ብቻውን የሀብት ወይም እድገት መለኪያ እንዳልሆነ አለም ተግባብቷል። ትክክለኛ እድገት መለኪያው ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል፣ የኑሮ ደረጃ መሻሻል፣ እንደ ውሀ፣ መኖርያ ቤት እና ኤሌክትሪክ ላሉ አገልግሎቶች ያለ ተደራሽነት... ወዘተ መሆናቸውን ራሱ Goldman Sachs ይጠቅሳል።

- የጋሪ እና ፈረስ ትራንስፖርት እናመጣለን እየተባለ ወደ ቀደመው ክፍለ ዘመን ወደኋላ ለመሄድ እየተንደረደርን

- በአለም ትላልቅ የሚባሉ ግጭቶች፣ ጦርነቶች፣ መፈናቀሎች እና ስደቶች እያስተናገድን

- የህዝብ የመኖር፣ የቤት ባለቤትነት፣ የስራ እና ተንቀሳቅሶ የማምረት አቅም እየተፈተነ... ወዘተ ባለበት ወቅት ይህን ትንበያ ይዞ ከካናዳ እና አውስትራልያ ልንበልጥ ነው ማለት ማደንዘዣ እንጂ ምንም ሊሆን አይችልም።

ብቻ መልካሙን ለሀገራችን እንመኛለን።

@EliasMeseret