Get Mystery Box with random crypto!

' አለ አይደል አንዳንዴ?...' ማለት አበዛለው!......... ውስብስብ..... ብናገር ሰው ሊረ | Ekutiinaa😍😘😍😘😉

" አለ አይደል አንዳንዴ?..." ማለት አበዛለው!......... ውስብስብ..... ብናገር ሰው ሊረዳው የማይችለው...ቢረዳውም ፈራጅ ይሆናል ብዬ ላሰብኩት ነገር......

የምመርጠውም የሚመጣልኝም ቃል ቢኖር " አለ አይደል አንዳንዴ? " የሚል ነው...... ብዙ ማስበውና የምደሰትበት ነገር አለኛ!..... ለሰሚ የሚያስገርም አይነት ለምን የሚል ጥያቄ የሚጭር አይነት.....እና እኔ ቀለል አደርግና.....ህመሙን ሀሴቱን ለራሴ በመተው
መናገር ሲከብደኝ " አለ አይደል..." እላለው!

አዋ! አለ አይደል አንዳንዴ ... ተንደርድረሽ እቀፊው እቀፊው ይለኛል .... ለምንስ ቶሎ ምንስ ቢፈጠር ሌላ አለም ውስጥ ካስገባሽ ክንዱ ትነጠያለሽ ይላል አካሌ........ ቀን ማታ ናፍቆቴ ነው ይኸው ደሞ ሁሉንም ሳልናገር ትቼው አለ አይደል ልል ነው....ቀርቦም እርቆም የሚናፈቅ ሰው ነው! .. አለ አይደል አንዳንዴ ........... እንዝላልነትም ሲጨመርበት ናፍቆት ይበረታል መሰለኝ!

አይኖቻችን በተገጣጠሙ ጊዜ አንገቴን ሰበር .... ወይም ዘወር ማድረግ ስራዬ ነው.... እወዳቸዋለው እፈራቸዋለሁም ........ከአፍህ ተቃራኒ እንዳይሆኑብኝ ይሆን? አሊያም ተመሳሳይ ሆኖ ብርቱነታቸውን እኔ ላይ እንዳያረጋግጡ? .......
ወይም ደግሞ የእኔን ዐይኖች ጓደኛህ እንዳይሆኑ ሰግቼ....... ደካማነቴን እንዳያሳብቁብኝ ፈርቼ...... አቃጣሪ እንዳይሆኑብኝ እና እያንዳንዷን ሀሳቤን ሹክ እንዳይሉህ ለማምለጥ......
እሸሻቸዋለው...... በየትኛው ምክንያት እንደሆነ ባይገባኝም ላያቸው፣ በጥልቀት ልመረምራቸው ፈልጌ እተወዋለሁ ........

አትኩረህ እንዳታየኝ ደግሞ ስስ ነህ ፈራሀለሁ!.....

@Ekutiinaa || @Ekutiinaa