Get Mystery Box with random crypto!

ጊዜው መሄዱ አይቀርም! በዚህ አለም ትልቁ ሽልማት ይሄ ቅፅበት ነው፤ ይቺ ቅፅበት ካለፈች አለፈች | 😍Best Profile Pictures😍

ጊዜው መሄዱ አይቀርም!

በዚህ አለም ትልቁ ሽልማት ይሄ ቅፅበት ነው፤ ይቺ ቅፅበት ካለፈች አለፈች ነው፤ ማንም አይመልሳትም። የማይጠቅምህን ወሬ ስትሰማ ወይ ተራ ቪዲዮ ስታይ ከእድሜህ ላይ 10 ደቂቃም ቢሆን ቀንሰህ እየሰጠሀቸው መሆኑን አስታውስ።

እድሜህን እንዴት በነፃ ትሰጣለህ?! የምናደንቃቸው ታላላቅ ሰዎች ከፍታው ላይ የወጡት ዕድሜያቸውን ለሚጠቅማቸው ነገር ሰጥተው ነው። አንተ ብታነብ ባታነብ ጊዜው መሄዱ አይቀር ፤ ብትሰራ ስራ ብትፈታ አመቱ ማለፉ አይቀር ፤ ብትማር ባትማር ደቂቃው መክነፉ አይቀር ፤ ወዳጄ የሚጠቅምህን አሳምረህ ታውቃለህ! ነገ የተሻለ ቦታ ለሚያደርስህ ነገር ቅድሚያ ስጥ!

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

Share -> @ei_du