Get Mystery Box with random crypto!

#ይመዝገቡ ፀሐይ ባንክ አ.ማ. በትሬኒ ባንከር የሥራ መደብ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው | EffoyJobs - Effoysira.com

#ይመዝገቡ

ፀሐይ ባንክ አ.ማ. በትሬኒ ባንከር የሥራ መደብ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ ተመዝግባችሁ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የኦንላይን ፈተና ወስዳችሁና ቅርንጫፍ ድረስ በመሔድ ሪፖርት ያደረጋችሁ ተወዳዳሪዎች፤ የመጨረሻ ዙር በአካል የጽሑፍ ፈተና በቅርቡ ይሰጣል፡፡

ስለሆነም ከዛሬ ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. እስከ አርብ ሚያዝያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. በሥራ ሰዓት በፀሐይ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት የሰው ኃይል አስተዳደር መምሪያ 5ኛ ፎቅ ወይም አቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ ፈተና የምትወስዱበትን ቦታ እንድትመርጡ እናሳስባለን፡፡

በተጠቀሱት ቀናት የምትፈተኑበትን ቦታ ያልመረጣችሁ ተወዳዳሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ሌሎች ዛሬ የወጡ ስራዎችን ከስር ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ
??
https://effoysira.com

Telegram:- https://t.me/effoyjobs