Get Mystery Box with random crypto!

ለትሬኒ ባንከር የሥራ መደብ አመልካቾች ፀሐይ ባንክ አ.ማ. በትሬኒ ባንከር የሥራ መደብ ሠራተኞች | EffoyJobs - Effoysira.com

ለትሬኒ ባንከር የሥራ መደብ አመልካቾች

ፀሐይ ባንክ አ.ማ. በትሬኒ ባንከር የሥራ መደብ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ ተመዝግባችሁ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የኦንላይን ፈተና ወስዳችሁ እና ቅርንጫፍ ድረስ በመሔድ ሪፖርት ያደረጋችሁ ስማችሁ ከስር በሊንኩ የተያያዘው ዝርዝር ላይ የተጠቀሳችሁ ተወዳዳሪዎች የመጨረሻ ዙር በአካል የጽሑፍ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡

ስለሆነም ከሚያዝያ 7 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. በሥራ ሰዓት በፀሐይ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት የሰው ኃይል አስተዳደር መምሪያ ወይም አቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ ፈተና የምትፈተኑበትን ቦታ እንድትመርጡ እናሳስባለን፡፡

ወደቅርንጫፍ በመሔድ የሚፈተኑበትን ቦታ በተጠቀሱት ቀናት ያልመረጡ ተወዳዳሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ሙሉ የስም ዝርዝሩን ለማየት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
https://effoysira.com/tsehay-bank-trainee-banker-candidates-name/