Get Mystery Box with random crypto!

አካታችነት (Inclusiveness) ምንድን ነው | Effoi እፎይ Assignment Helper

አካታችነት (Inclusiveness) ምንድን ነው
አካታችነት በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎችን ለመሳተፍ ወይም ለመወከል እንዲሁም ከእኩል እድል ተጠቃሚነት ጽንሰ-ሀሳብ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ አስተሳሰብ ነው።
አካታችነት በተለያዩ ግለሰቦች እና ቡድኖች መካከል ያለውን ልዩነት ለማቀራረብ እና ዋጋ ለመስጠት የሚሞክር ሂደት ሲሆን በተጨማሪም፣ አካታችነት፤ ግለሰቦችን ሙሉ በሙሉ አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ እና እንዲሳተፉ የሚያስችል ባህል እንዲፈጠር የሚያግዝ አስተሳሰብ ሆኖ ሊታይ ይችላል።
አካታችነት የተለያዩ ጉዳዮችን ወይም አካባቢዎችን የመሸፈን ወይም የመግባባት ብቃት ማለት ሲሆን የአካል ፣ የአዕምሮ እክል ወይም የሌላ አናሳ ቡድን አባል ለሆኑ ሰዎች እድሎችን እና ሀብቶችን በእኩልነት የማቅረብ ልምድ ወይም ፖሊሲ ይይዛል።
ስለ ማካተት ስናውራ ክታች የተጠቀሱትን ስድስት ነጥቦችን መመልከት አለብን
የተለያዩ ሃሳቦች በነጻነት እንዲገልጹ ማድረግ፣
ሁሉንም ማሳተፍ፣
ክፍት እና ቀጥተኛ ግንኙነት ማድረግ፣
አዳዲስ ሀሳቦች ክፍት በሆነ አእምሮ መቀበል፣
አስተማማኝና ጽኑ ውሳኔዎችን ማድረግ፣
ለጋራ እድገት አብሮ መስራት። ምንጭ፡ edi-toolkit.org @effoi_assignment_help