Get Mystery Box with random crypto!

what is Article Review ? የጽሑፍ ግምገማ ምንድን ነው? ከፍተኛ ጥልቅ ትንተና የሚ | Effoi እፎይ Assignment Helper

what is Article Review ? የጽሑፍ ግምገማ ምንድን ነው?
ከፍተኛ ጥልቅ ትንተና የሚጠይቅ እና በሚገባ የተዋቀረ አቀራረብን የያዘ የጽሁፍ አይነት ነው። የጽሁፍ ግምገማ በአንድ የተወሰነ መስክ ውስጥ ያሉ ጽሑፎችን በማጠቃለል፣ በመተንተን እና በማነጻጸር ወሳኝና ገንቢ ግምገማ ማድረግ ሲሆን የጽሑፍ ግምገማ፣ ጸሃፊው ያቀረባቸውን ሃሳቦች እና መረጃዎች በመለየት፣ ማጠቃለል እና መገምገምን ይጠይቃል። ይህንን ለማድረግ የሚከተሏቸው መመዘኛዎች እንደ አካዳሚ ዲሲፕሊን እና የምደባ መለኪያዎች መንገዶች ይለያያሉ።
እንደ Taylor and Francis (2023) ገለጻ ከሆነ የስነ-ጽሁፍ ግምገማ የተዛማጅ ጽሑፎች ግምገማ (Literature Review) ተብሎም ሊጠራ ይችላል። አላማውም በርዕሱ ላይ ስለ ወቅታዊ አስተሳሰብና አጠቃላይ እይታ መስጠት ሲሆን ከመጀመሪያው የምርምር መጣጥፍ በተለየ፣ አዲስ የሙከራ ውጤቶችን አያቀርብም።
የግምገማ ጽሑፍዎን መጻፍ ሲጀምሩ ግምት ውስጥ ማስገባት ያለብዎት 8 ነገሮች።
የመጽሔቱን ዓላማ እና ወሰን ማረጋገጥ
የጽሁፍን ወሰን መግለጽ
ለመገምገም ምንጮችን ማሰባሰብ
ርዕሱን፤ በረቂቅ እና ቁልፍ ቃላት መጻፍ
ርዕሱን ማሰተዋወቅ
ወሳኝ ግኝቶችን መጥቀስ
ማጠቃለል
የጻፍነውን ግምገማ ሌሎች ሃሳብ እንዲሰጡበት ማድረግ

ምንጭ: Essaypro.com, taylorandfrancis.com
@effoi_assignment_help