Get Mystery Box with random crypto!

ለተቋሙ ቁልፍ ደንበኞች አገልግሎት የሚሰጥ ነፃ የጥሪ ማዕከል ስራ ሊጀመር ነው የኢትዮጵያ ኤሌክት | Ethiopian Electric Utility

ለተቋሙ ቁልፍ ደንበኞች አገልግሎት የሚሰጥ ነፃ የጥሪ ማዕከል ስራ ሊጀመር ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተቋሙ ቁልፍ ደንበኞች አገልግሎት የሚሰጥ 904 የተሰኘ ነፃ የጥሪ ማዕከል ስራ ሊያስጀምር መሆኑን በተቋሙ የደንበኞች አገልግሎትና ቴክኒካል ሳፖርት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ካሴ ገለፁ፡፡

የጥሪ ማዕከሉ ከ160 ኪ.ዋ በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋሙ አስፈቅደው የሚጠቀሙ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ ለሆኑ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በጥሪ ማዕከሉ አገልግሎት የሚያገኙ 22,565 ቁልፍ ደንበኞችን የመለየትና ደንበኞቹ 904 የጥሪ ማዕከል ላይ መደወል እንዲችሉ ስልክ ቁጥራቸው ሲስተም ላይ እንዲተዋወቅ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ መሰል ተቋማትን የመለየትና የማካተት ስራ የሚከናወን ይሆናል ብለዋል አቶ መንግስቱ፡፡

በመሆኑም የ904 የጥሪ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጠው ከላይ ለተጠቀሱ ቁልፍ ደንበኞች ብቻ ሲሆን ሌሎች ደንበኞች በነባሩ የ905 የነፃ ጥሪ ማዕከል መገልገላቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ማዕከሉን የማደራጀትና ሰራተኞችን የመመደብ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጠው ይህ ጥሪ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጠው በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ቁልፍ ደንበኞች ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et