Get Mystery Box with random crypto!

አገልግሎቱ ለ35 የመስኖ ፕሮጀክቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ተደራሽ ማድረጉን ገለፀ በኢትዮጵያ | Ethiopian Electric Utility

አገልግሎቱ ለ35 የመስኖ ፕሮጀክቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ተደራሽ ማድረጉን ገለፀ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትግራይ ክልል ኤሌክሪክ አገልግሎት በ2015 በጀት ዓመት በክልሉ ለሚገኙ ለ35 የመስኖ ፕሮጀክቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገለፀ፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ካገኙት 35 የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል 26ቱ የግብርና ኢንቨስትመንቶች ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ በልማት ስራ ላይ የተሰማሩ የአርሶ አደር ማህበራት ናቸው፡፡

የመስኖ ፕሮጀክቶቹ ቀድሞ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የነበሩ ሲሆን በአካባቢው በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ተዘርግቶ የነበረው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጉዳት ስለደረሰበት አገልግሎቱ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም ፕሮጀክቶቹ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ 65 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ጥገና፣ 35 የተቃጠሉ ትራንስፎርመሮች ቅየራ እንዲሁም 45 ጉዳት የደረሰባቸው ቆጣሪዎች ጥገና በማድረግ ወደ ልማት እንዲገቡ ማድረግ ተችሏል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት በክልሉ 59 የመስኖ ፕሮጀክቶች ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በተመሳሳይ አገልግሎቱ በነባር የመካከለኛ መስመሮች ላይ የመልሶ ግንባታ ለማካሄድ ስራ የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በ32 መጋቢ መስመሮች ላይ በቅርቡ የተጀመረው ይህ ግንባታ የሚከናወነው 14 በግንበታ ላይ በተሰማሩ ማህበራት አማካኝነት ነው፡፡

የማሻሻያ ግንባታው ከሚከናወንባቸው መስመሮች መካከል ውቅሮ-አዲግራት-ብዘት፣ አቢአዲ ወርቅ አምባ፣ አክሱም - ሽረ፣ አድዋ - አክሱም፣ ሽቅሩማሪያም - ጭላ የመሳሰሉ መስመሮች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በዚህ የመካከለኛ መስመር የማሻሻያ ግንበታ ከዘጠኝ መቶ የማያንሱ ዜጎች በግንባታው የስራ እድል ተጠቃሚ ይሆናሉ የተባለ ሲሆን በግንባታው 12 ሺ የኮንክሪት መሰሶዎችን ለመትከል ዕቅድ ተይዟል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት