Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 የትምህርት ዘመን በሁሉም የትምህርት ተቋማት የትምህርት | Educate Ethiopia

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 የትምህርት ዘመን በሁሉም የትምህርት ተቋማት የትምህርት አጀማመርን በሚመለከት የሰጠው መግለጫ:-

የ2015 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስከረም 3 ቀን 2015 እንዲሁም የቅድመ እንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ እንደሚጀምር በወረደው የትምህርት ካላንደር መግለጻችን ይታወቃል።

ሆኖም ግን በከተማ ደረጃ ወጥ አድርጎ ማስጀምር በማስፈለጉ

1. ከመስከረም 26 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ለአጀማመሩ ሙሉ ዝግጅታቸውንያጠናቅቃሉ።

2. መስከረም 3 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርታቸውን ይጀምራሉ።

3. በሁሉም የትምህርት ተቋማት መስከረም 9 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ሃደት እንደሚጀምር አያሳስብን ክፍለ ከተማውም የትምህርት አጀማመሩን በጥብቅ ዲስፕሊን እንዲመራ አሳውቃለሁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ

via Temehert Bebete