Get Mystery Box with random crypto!

#ሀሰት_ነው ! ' ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ ' በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት | Educate Ethiopia

#ሀሰት_ነው !

" ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ " በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ ላይ ተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተናዎችን ለመውስድ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

ነገር ግን ማህበራዊ ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት ሆን ተብሎ ተማሪዎችን ለማዘናጋት በዘንድሮ ዓመት ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም ተብሎ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የወረደ አቅጣጫ የለም ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች " ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ" በሚል አሉባልታ ሳይምታቱ ለትምህርታቸው ትኩረት ስጥተዉ ለተሻለ ውጤት እንዲተጉ መልዕክት አስተላልፏል።

በተጨማሪ

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚኒስቴሩን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎች እየተለቀቁ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚሰረጩት መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን በማወቅ በትኩረት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አሳስቧል።

Via Tikvah