Get Mystery Box with random crypto!

ebstv worldwide📡☑️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebstvworldwide — ebstv worldwide📡☑️ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebstvworldwide — ebstv worldwide📡☑️
የሰርጥ አድራሻ: @ebstvworldwide
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 40.30K
የሰርጥ መግለጫ

Welcome to EBS TV WORLDWIDE Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates. Don’t forget to share it with your friends.
@ebstvworldwidebot
@EbswhatsnewBot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-04-21 19:53:32

2.6K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 19:53:24

2.2K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 19:53:13 #ሱዳን
የሱዳን የጦር ኃይል “አማፂ” ቡድን ብሎ በቅርቡ የፈረጀውን የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይል ወታደሮች በአስቸኳይ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ፡፡

የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት፣ መንግስት ከልዩ ኃይሉ ጋር አንዳች ድርድር እንደማያደርግ ሲገልፅ የልዩ ኃይሉ ወታደሮችም በአስቸኳይ እጅ እንዲሰጡ አዟል ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ጦር ያሳለፈው ውሳኔ የተኩስ አቁም በሱዳን እንዲደረግ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተጀመረውን ጥረት እንዳይጐዳው መሰጋቱ ነው እየተነገረ ያለው፡፡
በመዲናዋ ካርቱም በተለያዩ አካባቢዎች የከባድ መሳሪያዎች ድምፅ እንደሚሰማ እና ውጊያው ተባብሶ መቀጠሉ እየተዘገበ ነው ።
ዘገባው የአሶሼትድ ፕሬስ ነው ።

#የተናጠል የተኩስ አቁም
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይል ለ 72 ሰአታት የሚዘልቅ የተናጥል የተኩስ አቁም ማድረጉን አስታወቀ ።

በሀገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ለማቆም የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይሉ ለ72 ሰአታት የሚፀና የተናጥል የተኩስ አቁም ማወጁን ይፋ ሲያደርግ የሱዳን የጦር ኃይል ግን የተኩስ አቁሙን ለማድረግ አለመስማማቱ ነው የተዘገበው ።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የተኩስ አቁም ቢያወጅም በአገሪቱ ዛሬም ውጊያው ተባብሶ መቀጠሉ ነው የተነገረው፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለኢድ አልፈጥር በዓል ሲባል ተፈላሚ ኃይላቱ የሰብአዊ ድጋፍ መስጫ የግጭት ማቆም እንዲደረስ ተማጽነዋል ተብሏል።
ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው፡፡

#የአሜሪካ የመከላከያ ሰራዊት በጅብቲ
በሱዳን የቀጠለውን ቀውስ ተከትሎ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ተጨማሪ ወታደሮችን በጅቡቲ ሊያሰማራ እቅድ መያዙ ተነገረ፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በሱዳን በቀጠለው ግጭት ሳቢያ በካርቱም ያሉ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞችን ለማውጣት ሲባል የአሜሪካ ወታደሮች በጐረቤት አገር ጅቡቲ ሊሰማሩ መሆኑን ነው ይፋ ያደረገው፡፡
የአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢ ለአልጀዚራ እንዳሉት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ ጦር በጀቡቲ ለሚኖረው ስምሪት ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር በሱዳን ግጭት እየተፋለሙ ባሉት የሱዳን ጦር እና የልዩ ኃይሉ አመራሮች ላይ ማዕቀብ ሊጥል እያቀደ መሆኑ ነው የተሰማው፡፡
ዘገባው የአልጀዚራና ፎሪን ፖሊሲ ነው።

#ሕንድ
የሕንዱ የሴረም ተቋም ተስፋ የተጣለበትን አዲሱን 20 ሚሊዮን ብልቃጥ የ"R 21" የተሰኘውን የወባ ክትባት ለአፍሪካ ሀገራት ማቅረብ እንደሚችል አስታውቋል።

የሴረም ተቋም ለአፍሪካ 20 ሚሊየን የ “R 21” የተሰኘውን የወባ ክትባት በ2 ወራት ውስጥ ማቅረብ እንደሚችል የተነገረው 10 የአፍሪካ አገራት ለወባ ክትባቱ ፈቃድ ሊሰጡ በዝግጅት ላይ መሆናቸው እየተነገረ ባለበት ጊዜ ነው ።
ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡
2.1K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 19:53:05
#ሱዳን
የዓለም የጤና ድርጅት በሱዳን ለ7 ቀናት በቀጠለው ግጭት ከ400 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና ከ3 ሺ 5 መቶ የሚበልጡ ዜጎች ለጉዳት መዳረጋቸውን አስታወቀ።

የሱዳን ዶክተሮች ሲንድኬት የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በበኩሉ በሀገሪቱ 9 ሆስፒታሎች በቦምብ ፍንዳታ ሲጐዱ ካሉት 70 በመቶዎቹ የጤና ተቋማት በግጭት ውስጥ ባሉ አካባቢዎች በመሆናቸው አገልግሎት አቋርጠዋል ሲል ነው ያስታወቀው፡፡
የተመድ ዋና ፀሀፊ ቃለ አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ በሀገሪቱ ያሉትይ የጤና ተቋማት ሙሉ በመሉ ሊዘጉ በቋፍ ላይ በመሆናቸው አስቸኳይና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ይሻሉ ሲሉ ተናግረዋል ።
ዘገባው የሲቢሲ ኒውስ ነው፡፡
2.2K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 15:27:21

939 views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 06:01:30
ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው ዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ዒድ ሙባረክ መልካም በዓል!
2.1K viewsedited  03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:43:35

1.3K views17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:27:12 #ሱዳን
የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ለሁለተኛ ጊዜ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን አስታወቁ ።

የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ለሁለተኛ ጊዜ የግጭት ማቆም ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ነው በተናጥል ባወጡት መግለጫ ያስታወቁት ።
የዋይት ሐውስ የፕሬስ ጉዳዮች ኃላፊዋ ጂያን ፒሬ የጦር መሪዎቹ ለሁለተኛ ጊዜ ይፋ ያደረጉትን አበረታች የተኩስ አቁም ስምምነት ለማስከበር ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው።

#ሕንድ
የመንግስታቱ ድርጅት ሕንድ በአውሮፓውያኑ 2023 አጋማሽ አመት በሕዝብ ብዛት ቁጥር ቻይናን በልጣ የአንደኛነት ደረጃን እንደምትይዝ በትንበያው ይፋ አደረገ፡፡

ሕንድ አሁን ካላት ከ 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ በላይ ከወራት በኋላ አዲስ 2.9 ሚሊዮን ሕዝብ በመጨመር በሕዝብ ብዛት ከቻይና በልጣ የዓለም ቀዳሚዋ ሀገር እንደምትሆን ነው የመንግስታቱ ድርጅት ያስታወቀው ።
ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

#ስፔን
የስፔን ተመራማሪዎች በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ በሮቦት የታገዘ ውጤታማ የቀዶ ጥገና ህክምና ለአንድ የሳንባ ነቀርሳ ታማሚ ማካሄድ መቻላቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

የስፔን ተመራማሪዎች ለ65 አመቱ የሳንባ ነቀርሳ ታማሚ በሮቦት ያካሄዱት ቀዶ ጥገና ከዚህ ቀደም የተለመደውን የጐድን አጥንት በመስበር የሚካሄደውን ቀዶ ጥገና ያስቀረ እና ለቀዶ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚው ፍቱን እና ህመምን ያስወገደ ነው ተብሏል፡፡

“ዳ ቪንቺ” በተባለችው ሮቦት ለአዛውንቱ የሳንባ ነቀርሳ ታማሚ ቀዶ ያደረጉት የህክምና ቡድኑ መሪ ዶ/ር አልበርት ጃውሬጊዮ ይሄው መላ አዲስ ፣ ፍቱን እና የቅድመ እና ድህረ ቀዶ ህክምና ህመመምን ሁሉ የሚቀንስ ነው ብለዋል ።
የቀዶ ህክምና የተደረገላቸው አዛውንቱ በአገልግሎቱ ከህመማቸው የተሻላቸው መሆኑን እና አሁን ደስተኛ ነኝ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የቲ አር ቲ ወርልድ ነው፡፡
1.5K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:27:03
#ሱዳን
የዓለም የጤና ድርጅት በሱዳን ለ6ኛ ቀን በቀጠለው ግጭት በትንሹ 296 ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውንና 3ሺ የሚበልጡ ንፁሃን ሰዎች መቁሰላቸውን አስታወቀ።

በሱዳን ዋነኛ የጦርነቱ አውድማ ከሆነችው መዲናዋ ካርቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን መሸሽ መጀመራቸው ተነግሯል፡፡
"ዶክተርስ ሲንዲኬት" የተባለ የጤና ባለሙያዎች ቡድን ካርቱም እጅግ ከባድ ውጊያ ፣ ዘረፋ እና ሌሎች ወንጀሎች አየተፈፀመባት መሆኑን ነው ያስታወቀው::
የሱዳን ጦር በካርቱም እና በኦምድሩማን ከተማ በጦር አውሮፕላን በሚያካሂደው ድብደባ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሚጠቀምባቸውን የጦር ሰፈሮች መቆጣጠር መቻሉን ነው የተሰማው፡፡
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡
1.4K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 20:36:21

2.8K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ