Get Mystery Box with random crypto!

#ዩክሬን የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኤጀንሲ በአውሮፓ ትልቁ የሆነው በዩክሬን የሚገኘው የዛፓሮዢያ የኒው | ebstv worldwide📡☑️

#ዩክሬን
የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኤጀንሲ በአውሮፓ ትልቁ የሆነው በዩክሬን የሚገኘው የዛፓሮዢያ የኒውክለር ጣቢያ ደህንነት ጉዳይ አሳስቦኛል አለ።
የሩሲያ አስተዳዳሪዎች ከዛፓሮዢያ የኒውክለር ጣቢያ አካባቢ ካሉ ከተሞች የሚኖሩ ዜጐቻቸውን እና ወታደሮቻቸውን ለቀው እንዲወጡ ማድረጋቸውን ተከትሎ የዩክሬን ኃይሎች በአቅራቢያው በከፈቱት ጥቃት የዛፓሮዢያ የኒውክለር ጣቢያ አደጋ ውስጥ መሆኑን ነው የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤጀንሲ ይፋ ያደረገው ::
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ በዛፓሮዢያ የኒውክለር ጣቢያ አቅራቢያ በቀጠለው ግጭት ግዙፉ የኒውክለር ጣቢያ እጅግ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ መግባቱን ነው ያስታወቁት።
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡