Get Mystery Box with random crypto!

#ሩሲያ የቡድን 7 ሀገራት በግንቦት ወር በጃፓን በሚያካሂዱት ጉባኤ ላይ ከአውሮፓ እና ከቡድን 7 | ebstv worldwide📡☑️

#ሩሲያ
የቡድን 7 ሀገራት በግንቦት ወር በጃፓን በሚያካሂዱት ጉባኤ ላይ ከአውሮፓ እና ከቡድን 7 ሀገራት ወደ ሩሲያ በሚላኩ የወጪ ምርቶች ላይ ሙሉ ክልከላ እንዲጣል በሚያስችለው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሊመክሩ ማቀዳቸውን ሩሲያ ቱዴይ ዘግቧል፡፡በዚህም የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዚዳንት ዲምትሪ ሜድቬዴቭ የበለፀጉት የቡድን 7 አገራት ወደ ሩሲያ የሚላኩ የወጪ ምርቶች ላይ እገዳ እንዳይጥሉና ማዕቀብ የሚጥሉ ከሆነ ሩሲያ ከዩክሬን ወደቦች እህል እንዲወጣ ከተደረሰው ዓለም አቀፍ ስምምነት ትወጣለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል ።
#ሶማሊያ
የሶማሊያ መንግስት በአገሩ ተሰማርቶ ያለው የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል የቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ፍላጐት እንዳለው ይፋ አድርጓል።
የሞቃዲሾ መንግስት የሰላም አስከባሪ ኃይል “አትሚስ” የቆይታ ጊዜ እንዲራዘምለት ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የጐረቤት ሀገራት እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የማሳመን ሥራ እያካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሶማሊያ ፈቃደኝነት የተሰማው የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የፀጥታ ኮሚሽን በሶማሊያ ተሰማርቶ ያለውን የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል “አትሚስ” የቆይታ ጊዜ ላይ የፊታችን ረቡዕ ይመክራል ተብሎ በሚጠበቅበት ጊዜ ነው ።
ዘገባው የ ዘ ኢስት አፍሪካ ነው ።