ገላሽ ገላ አይመርጥም ፣ ከሁሉ ይጋደማል ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል ከሴት ክብርሽ ይልቅ ፣ ስሜትሽ ይቀድማል። ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ነግሬሽ ነበረ፡፡ ጭን ከሰማይ ቢገዝፍ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል ምን ተራራ ቢመስል... ጡትም አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡ ነግሬሽ ነበረ.... ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ የወንድ ልጅን ዐይን.. ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ ነግሬሽ ነበረ... ሴት ክብሯ የአምላክ ነው ፣ እንደ እናት ስታስብ!!! ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ነግሬሽ ነበረ... ክብረቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት በክብር ነው እንጂ. በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡ ።።።።። ነግሬሽ ነበረ እናትነት ስሟ ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ። ሴት ክብሯን ስታጣ ፣ እድሜዋ ይሔዳል የወንድ ልጅ ቤቱ... የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡ ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ነግሬሽ ነበረ... ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው ቁንጅናም ይረክሳል! ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው! ።።።። ነግሬሽ ነበረ ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ "ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ ልክ ነሽ አንዳንዴ እውነቶች ስሜት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ። ።።። ሞኝ ሰው ሲመክሩት ሞኝ ሰው ሲነግሩት የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ ግን እነግርሻለሁ! ነግሪያት ነበር ስል ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ። ።።። ግን እነግርሻለሁ ግን እመክርሻለሁ ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም ሁሉም ይተኛታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!! Belaya ሸጋ ቀን ይሁንላችሁ 40 views★ epaa , 05:45