Get Mystery Box with random crypto!

አንቺ ግን የለሽም ፣ ሰማዩን እያየው ከደመናው መሀል ጥርስሽ ይታየኛል ከንፋሱ ጋራ ሽው ከሚል | ኢbራhiም ለja

አንቺ ግን የለሽም ፣

ሰማዩን እያየው ከደመናው መሀል ጥርስሽ ይታየኛል
ከንፋሱ ጋራ ሽው ከሚል እጅብያ ሳቅሽ ይሰማኛል
አንቺ ግን የለሽም

ብቻዬ ጎዳናው እያቆራረጥኩት
ድንግት ከክንዴ ስር በጄ ተጠምጥሞ እጅሽን አሁት

አንቺ ግን የለሽም

የንጋት ብርሀን ብቅ ብትል ቤቴ
ከበሬ ! ሰንጥቃ ሾልካ ከማየቴ
አንቺን ነው ያሰብኩት

አንቺ ግን የለሽም

መምጣትሽን ናፍቄ አንቺ አልመጣሽም
እኔ ቃሌን ጠብቄ ቃልሽ አልሞላሽም
እኔ ስጠብቅሽ አንቺ ግን የለሽም

በ'ዕርግጥ ትመጫለሽ
ማረፊያሽ እኔ ነኝ
ባንቺ በመዘግየት ናፍቆትሽ ግን ጎዳኝ

ውዴ ሞላው አለም ከኔ ጋር ተቃርኖ
ሳቅሽን መስማት ብቻ ለኔ ፈውሴ ሆኖ
አንቺን ማየት ብቻ ለኔ መድህን ሆኖ
አንቺ ግን የለሽም
ስጠብቅሽ እኔ አንቺ አልመጣሽም

ኢብራሂም ለጃ