‹‹ጠ›› እና ‹‹ፀ›› ታገሬ ወጥቼ - ከተማ ገብቼ ገድ ቀናኝና - ካንቺ ተዋድጄ አልችል ብል ልለምደው - የከተማን ኑሮ በአነጋገሬ ላይ - አሰማሽ እሮሮ፤ ‹‹ፀሐይ›› አልኩ ብዬ - ‹‹ጠሀይ›› በማለቴ ‹‹ፀጉር›› ልል ፈልጌ - ‹‹ጠጉር›› የሚልን ቃል - ከአፌ በማውጣቴ ተበሳጨሽና - ቁጣ አዘነብሽብኝ በ‹‹አድርግ››ና ‹‹አታድርግ›› - ግማሽ ቀን ዋልሽብኝ፤ ‹‹ ‹ፀ› ማለት ሲገባህ - ‹ጠ›ን አትጥራ ሁሌ - ዳግም እንዳልሰማ እንዳታዋርደኝ - እንዳታስፎግረኝ - በነቃ ከተማ በቃህ አቁም በቃ - ዘወትር ‹ጠ› አትበል ‹ጠሎት›ንም ‹ፀሎት› - ‹ጠሀይ›ን ‹ፀሐይ› በል!›› ትዕዛዝሽን ላከብር - ምን ብጠነቀቅም ‹‹ጠ››ን በ‹‹ፀ›› ተክቼ - ተናግሬ አላውቅም፤ ይህን አየሽና… ‹‹ይቅር እንለያይ - በአንተ አልፈር እኔ ከብጤህ ተዛመድ - አቻ ሽቷል ጎኔ!›› ብለሽ ተለየሽኝ - ያላንዳች ይሉኝታ ባላወቅሁት ‹‹ቅጥበት›› - ባልገመትኩት አፍታ፤ ሳስበው አመመኝ… ሰበብሽ ያበግናል - ያጨሳል፣ ያደብናል ሰው እንዴት በቋንቋ - ፍቅርን ይመዝናል? ታዲያ ምኔ ዋዛ - ምኔ ሞኝ ነውና እኔም በተራዬ - እንተከተክ ጀመር - ‹‹ፀ››ን ተካሁኝና ይኸው ይኸውና … ‹ፅፍራም› ነሽ፣ ‹ገፃፃ› - ፍቅር የማይገባሽ ‹ፀብ› እንጅ መዋደድ - ‹ፄና› የሚነሳሽ እስኪ አሁን በሞቴ ምኑ ነው ‹ፅፋቴ›? በ‹ፀራራ› ፀሐይ - ‹ወክ› እናድርግ ማለቴ? ‹ፀርሙስ› ሙሉ ቢራ - በቀን ‹መፀፃቴ›? በ‹ፀፀር› ጎዳና - ‹ፀጅ› ይዤ ‹መውፃቴ›? ነው ወይስ ኮብልዬ - ከ‹ገፀር› ‹መምፃቴ›? በያ ንገሪኛ ምኑ ነው እሚያሳፍር - ይህ የኔ አማርኛ? እኔ ግን ልንገርሽ? በ‹ፀበልም› ባልድን - ባይለቀኝም ፍቅርሽ አብሮ መውፃት መግባት - ሰርክ ካሳፈረሽ ወይ ካሸማቀቀሽ ከእኔ ጋር መታየት - ከሰው ካሳነሰሽ ያውልሸ ጎዳናው - ሂጅ ወደፈለገሽ ‹ቢፄ›የን አላፃም ‹ፀብራራ›ው ‹ገፀሬ› - ‹ፃፃ› አለኝ መሰለሽ!! .......................... 412 views달콤한 , 19:55