Get Mystery Box with random crypto!

ለማህበሩ አባላት በሙሉ የበጎ ፍቃደኝነት ጥሪ ለአማካሪ ድርጅቶች CALL FOR VOLUNTEER CO | Ethiopian Association of Civil Engineers

ለማህበሩ አባላት በሙሉ
የበጎ ፍቃደኝነት ጥሪ ለአማካሪ ድርጅቶች
CALL FOR VOLUNTEER CONSULTING FIRMS
የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር በአገራችን በተከሰተው ጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በተሻለ ሁኔታ ዳግም እንዲገነቡ የሞያዊ ድጋፍ ለማድረግ እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ስለዚህም ከማህበሩ ጋር በበጎ ፍቃደኝነት ሙሉ የዲዛይን ስራ መስራት የምትፈልጉ አማካሪ ድርጅቶች የድርጅታችሁን ሙሉ መረጃ በ eacetraining@gmail.com subject label “Consulting Volunteer” በማለት እንድትመዘገቡ ማህበሩ ጥሪውን ያሰተላልፋል።

በቀጣይ ሳምንት ውስጥ ወደ ስራ መግባት የሚችል መሆን አለበት።
እናመሰግናለን