Get Mystery Box with random crypto!

በሴቶች ላይ የሚከሰት የሆርሞን መዛባት(Hormonal Imbalance) #የሆርሞን መዛባት የ | Dxn®_mart

በሴቶች ላይ የሚከሰት የሆርሞን መዛባት(Hormonal Imbalance)

#የሆርሞን መዛባት የሚከሰተው ሆርሞኖች በደም ውስጥ ከመጠን በላይ ከፍ ሲል ወይም ከመጠን በታች ሲሆን ነው። ሆርሞኖች ለህዋሳት፣ ለህብረ ህዋስ እና ለአካል ክፍሎችዎ ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያደርጉ በኢንዶክራይን (endocrine) እጢ የሚመረቱ ኬሚካሎች ናቸው። ሆርሞኖች በሰውነት ውስጥ ብዙ አስፈላጊ ተግባራትን ለመቆጣጠር ይረዳሉ፡፡

#የሆርሞን መጠን በመደበኛነት በተወሰኑ ጊዜያት ለምሳሌ ከወር አበባ በፊት ወይም በወር አበባ ወቅት ፣ በእርግዝና ወቅት ወይም በማረጥ ወቅት ይለዋወጣል ፡፡ የሆርሞን አለመመጣጠን በአድሬናሊን፣ ስቴሮይድ ሆርሞኖች፣ የእድገት ሆርሞኖች፣ ኢንሱሊን፣ ኢስትሮጅን ወይም ፕሮጄስትሮን በተባሉ ሆርሞኖች ላይ የተለመደ ነው።

#ምልክቶች

የምሽት ላይ ከፍተኛ ላብ
የጾታዊ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ
መሃንነት
የስሜት መለዋወጥ
ለመተኛት መቼገር
ድባቴ
የምግብ ፍላጎት ለውጦች (ቶሎ ቶሎ የርሃብ ስሜት መይም የምግብ ፍላጎት ማጣት)
ቶሎ ቶሎ የልብ መምታት
የጡት ህመም
የፊት ማበጥ
ራስ ምታት
የማተኮር ችግር
ክብደት መጨመር ወይም ክብደት መቀነስ
የቆዳ መድረቅ
የቆዳ ላይ ሽፍታ
አንገት ላይ እብጠት (እንቅርት)
የአጥንት መድከም
የፀጉር መሳሳት ወይም የፀጉር መርገፍ
ሙቀት ወይም ቅዝቃዜን አለመቻል
እይታ ላይ መቸገር
ለረጅም ጊዜ የቆየ ድካም

#በሴቶች ላይ የሚከሰት የሆርሞን መዛባት መንስኤዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ ፡-

ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ
ከመጠን በላይ ጭንቀት
ከፍተኛ የሰውነት ስብ
የፒቱታሪ ዕጢ ካንሰር
ዓይነት 1 እና 2 ዓይነት የስኳር ህመም
በዘር የሚተላለፍ የቆሽት ብግነት
በኢንዶክራይን (endocrine) እጢ ላይ የሚደርስ ጉዳት
በጣም ከባድ የሆኑ ኢንፌክሽን
ፀረ-አረም እና ፀረ-ተባይ ለሆኑ መድሃኒቶች መጋለጥ
ከባድ የአለርጂ ምላሾች
ተርነር ሲንድሮም
የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት
የወሊድ መከላከያ መድሃኒቶች
የሆርሞን ምትክ መድሃኒቶች
ኬሞቴራፒ ወይም ጨረር
የአዮዲን እጥረት
ሆን ተብሎ ወይም በፍላጎት ለረጅም ሰዓት ምግብ አለመውሰድ

#የሚደረጉ ምርመራዎች

የደም ምርመራዎች
የታይሮይድ ወይም የማሕፀንዎ እና የእንቁላል ማምረቻ የአልትራሳውንድ ምርመራ
የማህፀን ምርመራ
ራጅ
ኤምአርአይ (MRI)
ባዮፕሲ

#እንዴት በቤት ውስጥ በሰውነት ላይ የተከሰተውን ሆርሞን መዛባት ማስተካከል ይቻላል?

የአመጋገብን ሁደትን ማስተካከል
መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ
ስኳር እና ካርቦ ሃይድሬት ያላቸውን ምግቦች ማስወገድ
የተመጣጠነ ክብደት እንዲኖር ማድረግ
ጭንቀትን ማስወገድ
አረንጓዴ ሻይ መጠታት
በቂ የሆነ እንቅልፍ ማግኘት

#ህክምናው

ህክምናው መንስኤዎችን ያማከለ ነው፡፡
Reishi mushroom ይጠቀሙ።
@dxnmarket2