Get Mystery Box with random crypto!

መልዕክት ለዓረፋ በዓል ወደ ክፍለ ሀገር ተጓዦች። السلام عليكم ورحمة ا | የራህማን መስጂድ ደርሶች

መልዕክት

ለዓረፋ በዓል ወደ ክፍለ ሀገር ተጓዦች


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

አል-ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ እንኳን የ1443 ዓመተ-ሒጅራ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያ አስሩ ቀናቶች በሰላም አደረሳችሁ በማለት በተለያዩ የዒባዳ አይነቶች እንድትጠናከሩ ለማስታወስ ይወዳል።

በመቀጠል አመት-በዓሉን አስመልክቶ ለዚያራና ቤተሰብ ጥየቃ ወደ ተለያየ ቦታ እና ክፍለ-ሀገር የምትጓዙ ወንድምና እህቶች በሙሉ ስንጓዝ ሸሪዐን በጠበቀ መልኩ ሊሆን ይገባል። ወደ ቤተሰብ በምንጓዝበት ጊዜ ዓላማችን መብላትንና መጠጣት ላይ ብቻ ትኩረት ልናደርግ አይገባም።

ስለዚህ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ትክክለኛውን እስልምና በሰለፎች ግንዛቤ ላልደረሳቸው ማህበረሰቦች የማድረስ ግዴታ ይጠበቅብናል።

በመሆኑም የተለያዩ አጫጭርና ጠቃሚ የሆኑ ሪሳላዎች ማስቀራት የምንችል ኪታቦቹን በመያዝ ማህበረሰባችንን ልናስገነዝብ ይገባል።

ይህንን ማድረግ የማንችል አልፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ እንደተለመደው ወቅቱን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ኡስታዞቻችን ደርሶች ሙሀደራዎችንና እንዲሁም የተለያዩ ዲናዊ የሆኑ ትምህርቶችን በሚሞሪና በፍላሽ አዘጋጅቶ የሚጠብቃችሁ መሆኑን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው።

ማሳሰቢያ በራሳቸው ሚሞሪም ይሁን ፍላሽ በፈለጉት አይነትና መጠን ሲያስጭኑ ምንም አይነት ክፍያ የሌለው መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

{ምንም እንኳን በራሳችን መጣራትንና ማድረስ ባንችል በሌሎች ወንድሞች በኩል እንዲደርስ ሰበብ ሆነን የአጅሩ ተካፋይ እንሁን!}

አድራሻ አለም ባንክ ስልጤ ሰፈር ከፉርቃን መስጂድ ጎን ለጎን እንገኛለን

አልፉርቃን ኢስላማዊ እስቱዲዮ
የሰለፊዮች ድምፅ!


https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/10057