Get Mystery Box with random crypto!

Mental wellness የአእምሮ ጤና

የቴሌግራም ቻናል አርማ dryonaslakew — Mental wellness የአእምሮ ጤና M
የቴሌግራም ቻናል አርማ dryonaslakew — Mental wellness የአእምሮ ጤና
የሰርጥ አድራሻ: @dryonaslakew
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.67K
የሰርጥ መግለጫ

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 16:38:53

193 views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 06:01:17
314 views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 06:01:13 ህፃናት ለምን ሀይለኛ ይሆናሉ?
===================
አቡቲ 3 አመቱ ነው። እናቱ እንግዶች እያስተናገደች እሱ ኳስ ይጫወታል። ምሳ ካቀረበች በኃላ "ኳስ በቃ!" ብላ ኳሱን ወሰደችበት። እሪ ብሎ አለቀሰ ከዛም እናቱን መምታት ጀመረ። ስትይዘው ራሱን ከሷ ጋር ያጋጫል። ከእንግዶቹ አንዱ "ስጪው ይጫወት" ሲል በእድሜ ከፍ ያሉት "ፊት አትስጪው አልቅሶ ሲበቃው ዝም ይላል።" አሉ። ......

አብዛኞቹ ህፃናት ከ2-5 አመታቸው ላይ አልፎአልፎ ሀይለኝነት ሊያሳዩ ይችላሉ። የሚፈልጉትን ነገር ሲከለከሉ፣ በቂ ትኩረት ሳይሰጣቸው ሲቀር መሻታቸውን ለመግለፅ ቃላት ገና አላዳበሩም። በተጨማሪም ንዴትን መቆጣጠር እና በተገቢው መንገድ መግለፅ ስለሚያቅታቸው አልፎአልፎ ሀይለኛ ሊሆኑ ይችላሉ። የሶስት አመት ልጅ ተረጋግቶ "በኳስ እየተዝናናሁ ያለሁበት ሁኔታ ነው ያለው። የመጡትን እንግዶች አላውቃቸውም። ስለዚህ መጫወቴን ለምን ማቆም እንዳለብኝ አልገባኝም።" ሊል አይችልም።

ልጆች ሀይለኛ እንዳይሆኑና ከሆኑም ወላጆች ማድረግ የሚገባቸው ነጥቦች፦

1) መረጋጋት፦ ወላጆች ተረጋግተው ለልጆቻቸው ምላሽ ሲሰጡ ለልጆቻቸው ንዴትን መቆጣጠርን በተግባር ያሳዩአቸዋል። ከዛ ልጆች ፍላጎታቸውን እንዲናገሩ ማድረግ። ቃላት ካነሳቸው ማገዝ ቋንቋቸውን ስለሚያሳድግ በቀጣይ የሚፈልጉትን በንግግር መጠየቅ እንዲችሉ ያስችላቸዋል።

2) ትኩረት መስጠት፦ ለሚናገሩትና ለሚያደርጉት ነገር ትኩረት የሚሰጣቸው ልጆች የሚፈልጉትን በሀይለኝነት መግለፅ አያስፈልጋቸውም።

3) ፕሮግራሞችን ማሳወቅ፦ ነገሮችን ድንገት መከልከል ንዴት ይፈጥራል። ፕሮግራሞችን ማሳወቅ ግን የሚካሄደውን እንዲረዱና ምክኒያታዊ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። "ምሳ እስኪቀርብ መጫወት ትችላለህ።" ከዛ የተወሰነ ቆይቶ "ምሳ ሊቀርብ ስለሆነ ትንሽ የመጫወቻ ጊዜ ነው የቀረህ።"....

4) ምርጫ መስጠት፦ ልጆች እነሱን የሚመለከት ጉዳይ ላይ አማራጮች ሲሰጣቸው ሀላፊነት ይሰማቸዋል። በመጨረሻም የሚከለከሉት ነገሮች ላይ ምክኒያቱን መንገር ናቸው።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
307 views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 23:53:37 ሀይለኝነት
======
ፍሮይድ ሁሉንም የሰው ልጅ ፀባይ የሚነዳው ፅታዊ ፍቅር (Eros) ነው ብሎ ብዙ ሳይቆይ አንደኛው የአለም ጦርነት ይቀሰቀሳል፡፡ በጦርነቱ ላይ የተመለከታቸው ዘግናኝ ትዕይንቶች የሰዎችን ፀባይ የሚወስን ከፆታዊ ፍቅር ሌላ ሀይል እንዲገነዘብ አድርጎታል-ሀይለኝነት (Thanatos)፡፡ ሀይለኝነት ከሰው ውጭ ሌሎች እንሳሳትም ላይ ይስተዋላል፡፡ ሀይለኝነት በተገቢው ቦታና ሁኔታ ሲሆን በህይወት ለመቆየት አስፈላጊ ሲሆን ያለ ቦታው ሲሆን ከፍተኛ ጉዳት አለው፡፡

ዘመናዊነት የሀይለኝነትን ስሜት ቢያዳፍነውም ለማዳ ቢያደርገው እንጂ አያጠፋውም፡፡ የሀይለኝነት ምክኒያት ስነ ህይወታዊ ወይም ስነ ልቦናዊና ማህበረሰባዊ ሊሆን ይችላል፡፡ የሀይለኝነትን ስነ ህይወታዊ(ተፈጥሯዊ) ምክኒያቶች ለመረዳት ሁለት ልጆች ያሏትን እናት በልጆቿ መካከል ገና በህፃንነት ያለውን ልዩነት መጠየቅ በቂ ነው፡፡

ስነ ልቦናዊና ማህበራዊ ምክኒያቶቹ እንደሚከተለው ይከፋፈላሉ፡፡

1. መገልገያ፦ ሀይለኝነትን የሚያሳዩበት ዋና አላማ ክፋት ሳይሆን የሚፈልጉትን ለማግኘት ነው፡፡ ስጋ እየበላ ያለ ውሻ ሀይለኝነት የሚያሳየው ምግቡን ለመከላከል ነው፡፡ የማጅራት መቺ ሀይለኝነት አላማው ሌብነት ነው፡፡

2. ፍርሀት፦ አደጋ ሊደረርስ ከመሰላቸው እንስሳት ሀይለኛ ይሆናሉ፡፡ በሰዎችም በተመሳሳይ 'ማጥቃት መከላከል ነው !' በሚል በፍርሀት ምክኒያት ሀይለኝነት ሊኖር ይችላል፡፡

3. ድንበራዊ፦ ይህ አንዳንድ ጊቢዎች ውስጥ ከሚገኙት 'ሀይለኛ ውሻዎች' እስከ የታሪክ መፅሀፍትን የሞሉትን ጦርነቶች ላይ የሚታየውን ሀይለኝነት ያስረዳል፡፡ ድንበር!

4. ወንድነት፦ በአብዛኛው እንሳሳት ወንዶች ላይ የሚታይ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረግ ሀይለኝነት ነው፡፡ በሰው ላይ የሚታዩት ምሳሌዎች የአደባባይ ሚስጥር ስለሆኑ አልፌዋለሁ፡፡

ሀይለኝነት ላይ አካባቢያዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ልጆችን ሀይለኝነት ከሚያሳዩ ፊልሞችና ጌሞች መጠበቅ የወላጆች ሀላፊነት ሲሆን ከፍ ያለ ሀይለኝኘት ለሚያሳዩ ልጆች በማህበረሰቡ ተቀባይነት ባለው መልኩ በተለይ በስፖርታዊ ውድድሮች ላይ እንዲያውሉት ማገዝ ጥሩ ነው፡፡

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
458 views20:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:50:50

496 views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:13:04

540 views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:59:43

600 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 19:50:49

650 views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 06:46:20
629 views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 06:46:13 ዩዴሞኒያ 6- ሊዚ
===========
እናቷን ያዋለዳት ሀኪም የተወለደችው ልጅ ሲያይ ደነገጠ። እንደዛ አይነት ልጅ አይቶ አያውቅም። እናቷ እንዳትደነግጥ ልጇን አላሳያትም። ፎቶ አንስቶ ሰጣት። እናቷ ግን ምንም አልመሰላትም። ልጇን ማቀፍ ነው የፈለገችው።

እናትና አባቷ ሊዚ የተለየች እንደሆነች እንዳይሰማት አድርገው ነው ያሳደጓት። ትምህርት ቤት ስትገባ ተማሪዎች ይጠቋቆሙባታል፣ ያንሾካሽካሉ፣ ይሸሿታል። ሆናም ሊዚ ተቋቁማ አለፈችው።

ሰባተኛ ክፍል ስትደርስ የቤት ስራ ተሰጥቷት ልትሰራ ኢንተርኔት ከፈተች። "በyou tube ትንሽ ዘና ብዬ የቤት ስራዬን እሰራለሁ።" ብላ Youtube ውስጥ ስትገባ ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎች ያዩት ቪዲዮ ከላይ አለ። "የአለማችን እጅግ አስቀያሚዋ ሴት"The ugliest woman in the world ይላል። ስትከፍተው የእሷ ቪዲዮ ነው። ማን እንደቀረፃትና you tube ላይ እንደጫነው አላወቀችም። ለሊቱን ሙሉ ስታለቅስ አደረች።

ቆይታ ግን "እኔ ማለት ሰዎች የሚሉኝን አይደለሁም። ግሩም ድንቅ ነኝ። የሚሰድቡኝ፣ መጥፎ ነገር የሚናገሩኝ ሰዎች ማንነቴን እንዲወስኑ አልፈቅድላቸውም። ከድክመቴ ይልቅ ጥንካሬዬ ላይ ከጎደለኝ ይልቅ የተሰጠኝ ላይ አተኩሬ እሰራለሁ።" ብላ በተለቀቀው ቪዲዮ የተሸማቀቀችው ሊዚ ቪዲዮዎች እየሰራች ራሷ መልቀቅ ጀመረች። "ሰዎች ሲያዩኝ ምን ይላሉ?" ብላ በሀፍረት ቤት ትውል የነበረችው ሊዚ ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ንግግር ማድረግ ጀመረች።

ሊዚ ቬላስኬዝ አሁን ታሪኳን በመናገር ለሚሊዮኖችን ተስፋ፣ ጥንካሬ እና ፅናትን እያስተማረች ነው። እንደሊዚ አይነት ህመም ያለባቸው ሰዎች በጣት የሚቆጠሩ ይሁኑ እንጂ ሁሉም ሰው ድክመትና ጉድለት እንዳለው ሁሉ ዩዴሞኒያም አለው። በአካባቢው ያሉ ሰው ሰዎች ድክመቱ ላይ እንዲያተኩር ቢገፋፉትም ግለሰቡ ግን ጥንካሬና እምቅ ችሎታው ላይ የማተኮር ምርጫ አለው።

ዩዴሞኒያ ለሁላችንም!
545 views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ