Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​​​​​​​◈━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━◈ የደከመች እናት ፥ ዘመም ያለ | 💌የፍቅር ሕይወት™

​​​​​​​​​​​​​​​​​​◈━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━◈


የደከመች እናት ፥ ዘመም ያለ መንደር
ወረተኛ ፍቅር ፥ ተሰባሪ ወንበር
ሳስቶ ያለቀ ልብ ፥ ማጣት ያጠቆረው
ዳመና-አጥ ሰማይ ፥ ማልቀስ የቸገረው።

ብትወጣም ላትቀር ፥ ደስታ ቢስ ጨረቃ
ውሃ በፈረቃ፤
መብራት በፈረቃ፤
ራት በፈረቃ፤
የተለመደ ቃል ሳይጀመር 'በቃ'።

መጣ ያሉት ነዋይ ፥ ሳይታይ ይሸሻል
ነጋ ያሉት ሰማይ ፥ ጨልሞት ይመሻል
የዘመን ጥያቄ፤
መኖር ካለመኖር ፥ በምን እንደሚሻል።

እድሜ ዳገት ነገር
ሰው ሁሉ ላይጨርስ ሽቅብ የሚተነው
እድሜ ስቃይ ነገር
ያላነበበውን ያልቀሰመውን ነው የምትፈትነው።

ታምረኛ ዘመን፤
በታምር ላይ ታምር ፥ መደራረብ ያውቃል
እጅ አመድ አፋሽ ነው፤
የደሃ ሰው ጉልበት ፥ በገለባ ያልቃል
እረፍት አልባ ህይወት ፥ ሰው መሆይ ይጨንቃል።
ነገስ?...

እኔን ባይ

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅