Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

የቴሌግራም ቻናል አርማ drsofonias — ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias
የቴሌግራም ቻናል አርማ drsofonias — ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias
የሰርጥ አድራሻ: @drsofonias
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.60K
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም!!!
ይሄ ቻናል የተለያዩ መረጃ ምንለዋወጥበት ሲሆን ከዚህ በስተቀር ምንም አይነት የቴሌግራም ቻናል የሌለኝ መሆኑን በትህትና ገልፃለሁ!!
@DrSofonias

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 18

2022-07-15 19:50:21
1.3K views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 19:50:00 መጥፎ የሰውነት ጠረንን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?

የሰው ልጅ የራሱ የሆነ የተለየ የሰውነት ጠረን አለው። ይህ የሰውነት ጠረን ጤናማ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ግን ከመጠን ያለፈ ይሆንና ከራስ አልፎ ሌሎችንም ሊረብሽ ይችላል።

ሰውነታችን ኤክሶክራይን (Exocrine) እና አፖክራይን (Apocrine) የተሰኙ ሁለት አይነት ላብ አመንጪ እጢዎች አሉት።

ኤክሶክራይን የተባሉት እጢዎች በሁሉም የሰውነታችን ክፍል የሚገኙ ሲሆን የአፖክራይን እጢዎች ደግሞ ጉርምስና እና ኩርድናን በሚያመላክቱና ፀጉር በሚወጣባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው።

የአፖክራይን እጢዎች ፕሮቲንና ስባማ ንጥረ ነገሮችን ያመነጫሉ፤ ይህም ነው ለሰውነት ጠረን መፈጠር ምክንያት የሚሆነው።

የመጥፎ የሰውነት ጠረን መንስኤዎች

ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን እንደ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል እና ማጣፈጫዎችን አዘውትሮ መመገብ
ከላብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ባክቴሪያዎች

መፍትሄዎች

ንፅህናን መጠበቅ፤ በየቀኑ ሻወር መውሰድ በተለይም ካላበን በኋላ በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ
ሻወር መውሰድ ባንችል እንኳን ሰውነታችንን ማደራረቅ
ሙቀት በበዛባቸው ስፍራዎች የአየር ማቀዝቀዣዎችን መጠቀም
እንደ አየር ሁኔታው ሳሳ ያሉ ልብሶችን መልበስ፤ ሙቀት አፍነው የሚይዙ ኮተን ልብሶችን አለማዘውተር
ልብሶቻችን በተለይም የውስጥ ልብሶቻችን በአጭር ጊዜ ልዩነት መቀየር
ቅመም የበዛባቸውን ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ
ፀረ ባክቴሪያ የሆኑ ሳሙናዎችንና ጄሎችን መጠቀም
ዲዮድራንት ወይም የላብ ማጥፊያ ከመጠቀማችን በፊት ብብታችን ደረቅ መሆኑን ማረጋገጥ።

ከላይ የጠቀስናቸውን ሁሉ ተግባራዊ አድርገው የሰውነትዎ ጠረን የማይቀየር ከሆነ ግን ባለሙያዎችን ማማከር ተገቢ ነው።

ከሁሉም በላይ ግን ዘወትር ንፅህናችንን መጠበቅ ካልተፈለገ የሰውነት ጠረን ያድናል።

@DrSofonias
1.3K views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:54:20
1.9K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:53:59 የልብ ድካም ህመም

የልብ ድካም በአለማችን ቁጥር አንድ ገዳይ በሽታ ነው። በአለማችን ላይ በአመት ወደ ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በልብ ድካም ሳቢያ ህይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን በሃገራችንም ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሳሳቢ መልኩ እየጨመረ ይገኛል።

የልብ ድካም ሲከሰት ወደ ልብ ጡንቻ የሚዘዋወረው ደም በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የሚቋረጥ ሲሆን ወደ ልብ ህዋሳት መሄድ ያለበት ኦክስጅንና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ስለማይደርሱ የልብ የመምታት ስራ ይስተጓጉላል ማለት ነው።

የልብ ድካም በዋነኝነት መንስኤው የልብ ደም ስር መጥበብ ሲሆን በተጨማሪም የኦክስጅን እጥረት፣ የልብ ደም ስር መኮማተርና የልብ ቀዶ ህክምና ሌሎች የልብ ድካም መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ።

የልብ ደም ስር መጥበብ እንዴት ይመጣል?

የልብ ጡንቻዎች ደም በተገቢው መልኩ ወደ ሰውነታችን ለማድረስ ያልተቋረጠ ኦክስጅንና ሌሎች እንደ ግሉኮስ ያሉ ንጥረ ነገር ያስፈልጋቸዋል፤ ይህንንም ለማግኘት ቀጫጭን የሆኑ የልብ የደም ስሮች በልብ ጡንቻዎች መሃል ተዘርግተው ይገኛሉ።

አዘውትረን ቅባትና ስብ የበዛበት ምግቦችን የምንጠቀም ከሆነ እንደ ኮሌስትሮል ያሉ መጥፎ ስቦች በልብ ደም ስር ውስጥ መከማቸት ይጀምራሉ ፤ በጊዜ ሂደትም (እስከ 10 አመታት) የልብ የደም ስር መጥበብን ያስከትላል።

ከልክ ያለፈ ውፍርት፣ የደም ግፊት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ የስኳር በሽታ ለልብ ድካም ተጋላጭነትን ይጨምራሉ።

የልብ ድካም ምልክቶች

በልብ የደም ስር የተከማቸው ስብ በድንገት ተላቆ የደም ዝውውሩን ሲገታ የልብ ድካም ምልክቶች ይከሰታሉ። ምልክቶቹም ከሰው ሰው ሊለያዩ ይችላሉ፤ እንዲሁም በሴቶችና ወንዶች መካከል ሊለያይ ይችላል። የልብ ድካም ያጋጠመው ሰው የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያል።

የደረት ህመም፡ የህመሙ ደረጃ ከትንሽ እስከ ከባድ ሊሆን ይችላል፤
ታማሚው ደረቱ ላይ መክበድ፣ መጨምደድ፣ መግፋት ሊሰማው ይችላል፤
ህመሙ ከ3 እስከ 5 ደቂቃ የሚቆይ ወይም ሄድ መለስ የሚል ይሆናል ነገር ግን ህመሙ ከ10 ደቂቃዎች በላይ ከቆየ አስጊ ደረጃ የመድረሱ ማሳያ ነው።
የልብ ድካምን ህመም ከቃር ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ህመሙ የአቀማመጥ ቦታን በመቀያየር አይጠፋም።
የህመሙ ስሜት ወደ ትከሻ፣ የግራ እጅ፣ አገጭና አንገት መሰራጭት ሊኖረው ይችላል።
ለመተንፈስ መቸገር፣ ትንፋሽ መቆራረጥ፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፤
በላብ መዘፈቅ፣ ማዞርና ድንግዝግዝ ማለት፤
ማቅለሽለሽና ማስመለስ፤
ድካም ድካም ማለት፤
የሰውነት መገርጣት፣ ከንፈርና ጣቶች አካባቢ መጥቆር፤
ራስን መሳት ሌሎች የልብ ድካም ምልክቶች ናቸው።

የልብ ድካም ምልክቶች በሴቶች፣ በአዛውንቶች እና በስኳር ታማሚዎች ላይ የተለየ ምልክቶች ወይም ከነ ጭራሹም ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ።

የልብ ድካም እንዴት እንከላከል?

የደም ግፊት በትክክል መቆጣጥርና የታዘዘን መድሃኒት በትክክል መውሰድ፣
የተመጣጠነ የአመጋገብ ስርአት መከተል (ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ፣ የእጽዋት ተዋጽኦ ዘይቶችን…)
የኮሌስትሮል መጠን መቀነስ፤
ስኳር ህመም ካለ በአግባቡ ክትትል ማድረግ፣
አደንዛዥ ዕፅ ከመጠቀም፣ ሲጋራ ከማጨስ፣ አልኮል ከመጠቀም መቆጠብ
ከመጠን ያለፈ ውፍረት ማስወገድ እንዲሁም አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል።

@DrSofonias
1.9K views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:43:22
የማቀፍ የጤና ጥቅሞች

የኦክሲቶሲን መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። የኦክሲቶሲን (Oxytocin) መጨመር የብቸኝነት፣ የመለየት እና የንዴት ስሜትን ለማስወገድ ይረዳል።
ረዘም ላለ ጊዜ ተቃቅፎ መቆየት የሴሪቶኒን (Serotonin) መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። ይህም ሙድን በመጨመር የደስታ ስሜትን ያጎናጽፋል።
የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋል።
ጡንቻዎቻችን ዘና እንዲሉ ያደርጋል።
ህመም ወይም በሽታ ከእርስዎ እንዲርቅ ያደርጋል።
ወደ ለስላሳ የሰውነት አካሎች የደም ፍሰትን በመጨመር ህመምዎን ያስታግሳል።
የነርቭ ሥርዓትን ያመጣጥናል።
መተቃቀፍ መመሰጥ እና ሳቅን ይተካል።
ግጭትንና ውጥረትን (ጥልን) ያረግባል። (ጥል ከመጀመሩ በፊት ቢሆንም እንኳን)።
በልጅነት ወቅት መታቀፍ እና ፍቅር፤ ልጆች ጤናማ ሆነው እንዲቆይ ያደረጋል።
ከአንድ በላይ በሆነ መንገድ ለልብዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው።

መልካም ጤንነት!!

@DrSofonias
2.3K viewsedited  14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:04:13
ወንዶች የመራባት እድላቸውን እንዴት መጨመር ይችላሉ?

ጭንቀት፣ ውጥረት እና ድካምን መቀነስና መቆጣጠር።
ሲጋራ እና የአልኮል መጠጦችን ያቁሙ።
ጤናማ እና የተስተካከለ የሰውነት ክብደት ይኑርዎ።
ከፍተኛ የዚንክ መጠን ያላቸው ምግቦች (ሥጋ፣ እንቁላል፣ ጥራጥሬዎችና የባህር ውስጥ ምግቦች) እንዲሁም ሰሊኒየም (የባህር ውስጥ ምግቦች፣ እንጉዳይ፣ ስጋና ለውዝ) እንዲሁም ቫይታሚን ኢ ይመገቡ።
በቻሉት መጠን የሃፍረተ ስጋ ፍሬዎ (Testicles) እንዲቀዘቅዙ ያድርጉ። ከዛሬ ጀምሮ ረዘም ላለ ጊዜ ሙቅ ሻወር እና ሳውና ባዝ አይውሰድ ምክንያቱም የስፐርም (Sperm) ሴሎችን ቁጥር ስለሚቀንስ ነው።

መልካም ጤንነት!!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤

@DrSofonias
2.6K viewsedited  14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:38:41
2.9K views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:38:14 በቂ ፋት እያገኙ እንዳልሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች

ፋት ያለባቸው ምግቦች ብዙውን ግዜ በመልካም ጎኑ ስማቸው ሲነሳ አይሰማም። ነገሩ እንዳለ ሆኖ ግን ፋት ያለበት ምግብ መመገብ ብቻውን የሰውነት ክብደታችን ያለመጠን እንዲጨምር አያደርግም። በአግባቡ እስከተመገብን ድረስ።

ሰውነታችን በተፈጥሮው ፋት ይፈልጋል። ሰውነታችን የሚፈልገውን የፋት መጠን በአግባቡ ካልሰጠነው በጤናችን ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ያስከትላል። ሰውነታችን በቂ መጠን ያለው ፋት ሳያገኝ ሲቀር የሚከሰቱ ምልክቶች አሉ። ከእነዚህ ምልክቶች መካከል የሚከተሉት አምስቶቹ ዋነኞቹ ናቸው።

1. የቫይታሚን እጥረት (Vitamin deficiencies)

እንደ ቫይታሚን ኤ፣ ዲ፣ ኢ እና ኬ (A, D, E & K)የመሳሰሉ የቫይታሚን አይነቶች በፋት የሚሟሙ (fat soluble vitamins) ይባላሉ። ሰውነታችን እነኚህን ቫይታሚኖች መጦ ለመጠቀም የፋት ይዘት ያላቸው ምግቦችን ማግኘት ይፈልጋል። ይህ በማይሆንበት ግዜ የእነዚህ ቫይታሚኖች እጥረት ሰውነታችን ይገጥመውና ለሚከተሉት የጤና እክሎች ልንጋለጥ እንችላለን:-

በምሽት ለማየት መቸገር (night blindness)
የጸጉር ድርቀት (dry hair)
መሃንነት (infertility)
የጡንቻ ህመም (muscle pain)
ድብርት (depression)

2. የቆዳ መቆጣት (Dermatitis)

የኤን ሲ ቢ አይ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ፋት የቆዳ ጤንማነት ላይ ትልቅ ድርሻ አለው። በቂ የሆነ ፋት ካላገኘን ሰውነታችን ዴርማቲቲስ ለተባለው ለቆዳ መቆጣት በሽታ የመጋለጥ እድላችን ሰፊ ነው።

3. የቁስል በቶሎ ያለመዳን

በፋት እጥረት ምክንያት እንደ ቫይታሚን ኤ እና ዲ የመሳሰሉ ቫይታሚኖች እጥረት ሊከሰት ይችላል። ይህም እነኚህ ቫይታሚኖች በቁስል በቶሎ መዳን ላይ ያላቸውን ሚና ስለሚያሳጣን የቁስል በቶሎ ያለመዳን ችግር ሊከሰት ይችላል።

4. የጸጉር መነቃቀል

ፕሮስታግላንዲንስ (Prostaglandins) የተባሉ የፋት ሞለኪውሎች በጸጉር እድገት እና ጤናማነት ላይ ትልቅ ድርሻን ይጫወታሉ። በቂ ፋት ያለመመገብ ይህን ፋቲ ሞሎኪውል በበቂ መጠን እንዳናገኝ ስለሚያደርግ ለጸጉር ወዝ ማጣት እና የመነቃቀል ችግር ሊያጋልጠን ይችላል።

5. ተደጋጋሚ ህመም

በበቂ መጠን ፋት ያለማግኘት ሰውነታችን ሊኖረው የሚገባውን የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity) ይጎዳል። ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅሙን ለማደበር ከሚፈልጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ፋት ነው። ይህም በመሆኑ በቂ ፋት አለመመገብ ደካማ የበሽታ መከላከል ስረዓትን በማዳከም በቀላሉ ለበሽታዎች የምንጋለጥበትን እድል ይፈጥራል።

ጤናማ ፋት ያላቸው ምግቦች የትኞቹ ናቸው?

ፋት መመገብ ሲባል የግድ ጮማ ስጋ መቁረጥ ማለት አይደለም። በቀላሉ የፋት ይዘት ልናገኝባቸው ከምንችልባቸው ምግቦች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ:-

አቮካዶ
እንቁላል
አሳ
ለውዝ
እርጎ
ኦሊቭ ኦይል

@DrSofonias
2.9K views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 11:12:58
2.5K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 11:12:25 ክብደት ለመጨመር ምን ላቁም? ምንስ ልመገብ?

ክብደት መጨመር ክብደት ለመቀነስ ከሚደረገው ተግባር እኩል ተመሳሳይ ትጋት ይፈልጋል። ትክክለኛውን አመጋገብ በመምረጥ ደግሞ ምንም የማናሳካው ግብ አይኖርም።

እርግጠኛ መሆን የሚቻለው ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሰዎች ተጨማሪ ክብደት የሚያገኙባቸውን አማራጮች ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት ያድርባቸዋል። ውፍረት ከሽብር አደጋ ባልተናነሰ የዓለማችን ስጋት በሆነበት ዘመን የተስተካከለ አቋም እንዲኖረን በርካታ ጥረቶችን እናደርጋለን።

በተመሳሳይ ሁኔታ ከልክ ባለፈ ሁኔታ ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሰዎችም፣ ለበሽታ ሊኖራቸው የሚችለውን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ ለብሰው እንዲያምርባቸውና በሂደቱ ሊከሰትባቸው የሚችለውን ምቾት ማጣት ለማስወገድም እንዲሁ፣ ተጨማሪ ክብደት በሰውነታቸው ላይ ለመጨመር የመፍትሄ በሮችን ሁሉ ያንኳኳሉ።

ባለሙያዎች ታዲያ ከመፍትሄ አቅጣጫዎች የምናገኘው ስብ ወይስ ጡንቻ የሚለውን ቀድመን መለየት እንዳለብን ያስገነዝቡናል። አንዳንዶቹ በሰውነታቸው ላይ ስለሚጨምሩት ክብደት ትኩረት አይሰጡም። ጡንቻ፣ ስብ ወይም የሁለቱ ጥምረት፤ እነዚህ ሰዎች ከብዶና ወፍሮ መታየት ብቻ ስለሆነ ዓላማቸው ወደ ባሰ ሁኔታ ሊሸጋገሩ ይችላሉ።

ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች በተሻለ ሁኔታ ክብደት በሰውነታቸው ላይ መጨመር ስለሚችሉበት መንገድ፣ ከምርምር ውጤቶች የተገኙትን እነዚህ መመሪያዎች በተቻለ መጠን ለመተግበር እንሞክር፡፡

በቀን 5-6 ጊዜ መመገብ

ክብደት ለመጨመር በቀን ከ5 እስከ 6 ጊዜ መመገብ መጀመር ይኖርብናል፡፡ ታዲያ የመመገቢ ሰዓታችን በሚገባ መከፋፈል ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም በአንድ ጊዜ በምንወስደው ከፍተኛ ምግብ ሳቢያ ጨጓራችንም በስርዓት መፍጨት እንዳይችልና ሰውነታችን ሁሉንም ካሎሪዎች መቀበል እንዳይችል ምክንያት ይሆናል።

እርግጥ ነው በየ3 ሰዓታት ልዩነት የምግብ ፍላጎታችን ላይነሳሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን ጫን ብለን መመገባችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡ በየዕለቱም የምግብ ፍላጎታችን እያደገ ስለሚመጣ፣ መቸገራችን ይቀንሳል፡፡ በተቻለ መጠን ታዲያ በአመጋገባችን ውስጥ ጤናማ ምግቦችን መምረጣችንን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡

ክብደት የማንሳት ልምምዶችን በሳምንት ሶስት ጊዜ ማድረግ

በክብደቶች በመታገዝ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ስንጀምር ጡንቻዎቻችንን ማሳደግ እንችላለን፡፡ በሂደትም የክብደቶቹን ሚዛን መጨመር ያስፈልጋል፡፡ ይሄ በተለይ ከሰውነት ክብደታችን ባሻገር ጥንካሬያችንን ማሳደግ እንድንችል የሚረዳን ነው፡፡

ከ300-500 ካሎሪዎችን ማከማቸት

ቀደም ሲል እንደተገለፀው፣ ከ300-500 የካሎሪ መጠን ማከማቸት የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ የሚያደርገን ከሆነ መሞከሩ አይከፋም፡፡ ይሄንን የካሎሪ መጠን ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ ነው ማግኘት የምንችለው፡፡

ሁሉንም የሰውነት ክፍል ማሰራት

በጂም ወይም በቤት ውስጥ ስፖርት የምንሰራ ወይም ክብደት የምናነሳ ከሆነ ሁሉም የሰውነት ክፍላችን በሚገባ እየሰራ መሆኑን ነው በቅድሚያ ማረጋገጥ ያለብን።

ምክንያቱም ብዙዎቻችን ትኩረት የምናደርግባቸው ብዙ የጡንቻ ክፍሎች አሉንና ስፖርቱን የሚጀምሩ ብዙ ሰዎች በአንገታቸው፣ ደረታቸው ወይም ማጅራታቸው አካባቢ ብቻ ትኩረት በመስጠት ልምምድ በማድረግ ትልቅ ስህተት ይፈጽማሉ።

ይሄ አካሄድ የሰውነታችን ሚዛን እንዲበላሽ በማድረግ ሰዎች የማይወዱትን ሰውነት እንድንላበስ ምክንያት ይሆናል።

በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር

ቀደም ሲል እንደተገለፀው ከ300-500 የካሎሪ መጠን ማከማቸት፣ የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ የሚያደርገን ከሆነ ይሄንን የካሎሪ መጠን ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ ነው ማሳካት የምንችለው፡፡

ካሎሪዎች መጠጣት

የተጠየቅነውን ካሎሪ በመብላት ብቻ ሟሟላት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ወተትና የወተት ተዋፅኦዎችን፣ እንዲሁም አነስተኛ ስኳር ጋር በፕሮቲን የበለፀጉ መጠጦችን ነው ማዘውተር ያለብን፡፡

በፍጥነት መመገብ

ይሄ ምክር በተቃራኒ ውፍረታቸውን መቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች የሚታዘዝ ነው። ሰውነታችን በቂ ምግብ ስለማግኘቱ ምላሽ እንዲሰጠን የተወሰኑ ጊዜዎችን ይፈልጋል። ስለዚህ በፍጥነት መመገባችን ከሰውነታችን የጥጋብ ምልክት ከማግኘታችን አስቀድመን ብዙ እንድንመገብ ያደርገናል።

ለማገገሚያ የተለያዩ አማራጮችን መከተል

የማፍታቻ እንቅስቃሴዎች፣ ሻወር፣ በካርቦ-ሃይድሬት የበለፀጉ ምግቦች ሰውነታችን በፍጥነት እንዲያገግም ያደርጋሉ። ታዲያ የ8፡00 ሰዓት እንቅልፍ እንዳይዘነጋ።

በራሳችን ላይ ትዕግስት ይኑረን

ጤናማ ባልሆነ አካሄድ በፍጥነት ተጨማሪ ክብደትን ማግኘት ተጨባጭ አይደለም። የተቀመጡ መመሪያዎችን በመከተል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ1-2 ኪሎ ብቻ ነው ማግኘት የሚቻለው። ባለሙያዎች ፈጣን ለውጥ ካላገኘን በቀላሉ ስሜታችን ሊጎዳብን አይገባም ይሉናል። ምክንያቱም የሁሉም ሰው ሰውነት ልዩነት ስላለው።

በራስ መተማመን

ክብደት ለመጨመር ያወጣነው ዕቅድ ክብደት የሚለካው ለስኬታማነቱ በራሳችን ላይ ያለን መተማመን ነው። ከጠንካራ ሥራ በኋላ ለውጥ ማየት ባንችልም፣ ሌላና እጅግ ጠንካራ ወደ ሆነ ልምምድ መግባት ይኖርብናል።

ተጨማሪ ምግብ መመገብ፣ ተጨማሪ ክብደቶችን ማንሳት፣ የውስጥ ጥንካሬን አስጠብቆ መቆት ናቸው፣ ክብደት መጨመር ከሚፈልግና በራሱ ከሚተማመን ሰው የሚጠበቀው፡፡

ረዥም ርቀት መሮጥ ውጤት የለውም

መሮጥ ግዴታ ከሆነ አጫጭር ርቀቶችን እና አቀበቶችን መውጣት ነው ተመራጩ። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የአጭር እና ረዥም ርቀት ሯጮችን ሰውነት መመልከት ነው። የትኛውን ነው መሆን የምፈልገው? በማለት ራስን መጠየቅ ደግሞ መሰረታዊ ነው።

መተኛት

ከፍተኛ ክብደት ለመጨመር በቀን ቢያንስ 8 እና 9 ሰዓት መተኛት ጥሩ አማራጭ ነው። ሰውነታችን ምንም ስራ እንዳይሰራ በማድረግ በተኛበት ጡንቻ እንዲገነባ እናስችለዋለን። በቀን ውስጥ ከ6 ሠዓት እና ከዚያ በታች እንቅልፍ እያገኘን ከሆነ፤ በአመጋገባችንና በስፖርት እንቅስቃሴዎች ያመጣናቸውን ለውጦች ማስጠበቅ አንችልም።

@DrSofonias
2.5K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ