Get Mystery Box with random crypto!

+ ወርቃማዎቹ አባቶቻችን እንዲህ አሉ + 'ሰዎች የሚያብዱበትና እንደነሱ ያላበደ ሰው ሲያዩ 'እ | ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜ ፀጋ ዮሐንስ

+ ወርቃማዎቹ አባቶቻችን እንዲህ አሉ +

"ሰዎች የሚያብዱበትና እንደነሱ ያላበደ ሰው ሲያዩ "እንደኛ ስላልሆንክ አብደሃል" የሚሉበት ዘመን ይመጣል"
ቅዱስ እንጦንዮስ
"እግዚአብሔርን ከግርማው ታላቅ የተነሣ ብቻ አትፍራው:: ከፍቅሩ ታላቅነት የተነሣ ፍራው"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ


"የጥበብ መጀመሪያው እግዚአብሔርን መፍራት ነው:: የጥበብ መጨረሻው እግዚአብሔርን ማፍቀር ነው:: የመጨረሻው ደረጃ ላይ ስትደርስ እግዚአብሔርን ከመፍራት ወደ ፍጹም ፍቅር ትደርሳለህ:: ፍቅር ፍጹም ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላልና" ቅዱስ እንጦንዮስ ዘየዓቢ


"ለልጆችህ ስለ እግዚአብሔር ከምትነግራቸው የበለጠ ለእግዚአብሔር ስለ ልጆችህ ንገረው"
አባ ኤጲፋንዮስ ዘአቴና

"እውነተኛ እውቀት የትሕትና ፏፏቴ ነው"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ


"ጌታ ጴጥሮስን በባሕር ላይ ሊወድቅ ሲል በሚታይ እጁ የያዘው በየብስ ላይ በማይታይ እጁ እንደያዘው ለማስተማር ነበር" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

"ክርስትና እጅግ ኃያል የሚሆነው በዓለም በተጠላ መጠን ነው" ቅዱስ አግናጥዮስ

"ይህንን ካስታወስክ በሰው መፍረድ ታቆማለህ:: ይሁዳ ሐዋርያ ነበር:: ከጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ነፍሰ ገዳይ ነበር" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ