Get Mystery Box with random crypto!

አጠቃላይ የስብሰባ ጥሪ ለአዲስ ተስፍ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከብሎክ (497-507)የቤት ባለዕድለ | 13ኛ ዙር 20/80 ኮንዶሚኒየም ባለቤቶች መብት ሞጋች ህብረት

አጠቃላይ የስብሰባ ጥሪ
ለአዲስ ተስፍ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከብሎክ (497-507)የቤት ባለዕድለኞች እና ህጋዊ ዉክልና ያላችሁ በሙሉ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን ሰኔ 26/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3:00 ሰዓት ላይ አጠቃላይ ስብሰባ በግቢያችን ውስጥ ስለሚደረግ እንዲሁም በዕለቱ የሚቀርቡ የመወያያ አጀንዳዎች ውስጥ በጥቂቱ
1.በማህበሩ እስካሁን ድረስ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር ማቅረብ።
2.ስለቀሪ የግንባታ አፈፃፀም በተለይ የጣራ ችግሮች
3.ማህበሩ በቀጣይ ሊሰሩ የታቀዱትን ስራዎች ለህዝቡ ማሳወቅ
4.ስለሰርብለስ አወጋገድ
5.ስለልማት ወርዓዊ ክፍያ አከፋፈል
6.ስለ ለሳንተሪ አሰጣጥ ለመወያየት ወሳኝ ስብሰባ ስለሚኖረን ለመብታችን በጋራ ለመቆም ሁላችንም እንድንገኝ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ። አስታውሱ ይህ ጉዳይ የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የቤት ባለዕድለኞች ጉዳይ ስለሆነ ሁላችንም በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት እንድትገኙ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን ።



ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው