Get Mystery Box with random crypto!

የስብሰባ ጥሪ ለ13ኛው ዙር የቤት የቤት ባለእድለኞች በሙሉ እንደሚታወቀው ከሶስት አመት በፊት የ | 13ኛ ዙር 20/80 ኮንዶሚኒየም ባለቤቶች መብት ሞጋች ህብረት

የስብሰባ ጥሪ ለ13ኛው ዙር የቤት የቤት ባለእድለኞች በሙሉ
እንደሚታወቀው ከሶስት አመት በፊት የካቲት 27 ቀን 2011ዓ.ም የ13ኛው ዙር የ20/80 ፕሮግራም ለቤት ባለ እድለኞች በወጣው ዕጣ መሰረት ቤት ደርሶን በተስፋ ቤታችን እንዲሰጠን ስንጠብቅ ቆይተን በተለያዩ ምክንያቶች በዕጣ ያገኘነውን ቤት ለመረከብ ባለመቻላችን በመሰባሰብ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ በመሄድ ጥያቄ በማቅረብ፣ በኋላም ጥያቄያችንን በተቀናጀ መልክ ለማቅረብ ይቻል ዘንድ ከባለእድለኞች መካከል በራስ ተነሳሽነት የተወሰንን ግለሰቦች በኮሚቴነት በመደራጀት የባለእድለኞችን ጥያቄ በመያዝ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ጋር በመነጋገር በርካታ እልህ አስጨራሽ ጥረቶችን በማድረግ የቤት ባእድለኞችን ውል በማዋዋል የቤት ባለቤትነት ህጋዊ ሰነድ ያገኘንበትን ሁኔታ መፍጠር መቻሉ ይታወቃል፡፡
ከዚያም በኋላ በፕሮጀክትና በፓርሴል በመደራጀት በተደጋጋሚ በጋራ የመኖሪያ ቤታችን የግንባታ ሂደት መጓተት፣ የግንባታ ጥራት ችግር፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ግንባታ መጓተት፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም ባልገባንበት ቤት የምንከፍለው የባንክ ብድር ወለድ ይነሳልን ጥያቄ ስናነሳ ቆይተናል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አብዛኛው የቤት ዕድለኞች ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮ የሚኖሩ በመሆናችን ለብዙ ችግር ተዳርገናል፡፡ በመሆኑም አብዛኛው ነዋሪ ከፍተኛ የወለድ ጫና እና ከፍተኛ የቤት ኪራይ ክፍያ መክፈል ባለመቻሉ ባልተጠናቀቀ ቤት እና ባልተሟላ መሰረተ-ልማት ውስጥ በደረሰው ቤት ውስጥ አንድ ጀሪካን ውሃ በ40 ብር እየገዛ ወደ ፎቅ ለማስወጫ ደግሞ ሌላ ክፍያ እየተጠየቀ በመኖር ላይ ይገኛል፡፡ ይህንን የሁላችንንም የጋራ ጥያቄዎች፣ አቤቶታቸውን፣ ምሬታቸውንና ቅሬታቸውን አቅርበናል:: ይሁንና ለጥያቄያችን ተገቢውን ምላሽ ማግኘት ባለመቻላችን ጉዳዩን ወደ ሚዲያ ማውጣት ግዴታ ሆኖብናል፡፡
ስለሆነም እንደ13ኛ ዙር ባሉን መሠረታዊ የጋራ ችግሮቻችን ዙሪያ በ29/08/2014ዓ.ም ስብሰባ ስለሚኖረን በዚሁ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጡን የተለያዩ የሚዲያ ተቋማትን ያነጋገርን በመሆኑ በእለቱ ጠዋት 2:30 ሰዓት ላይ ፕሮጀክት 18 ልዩ መጠሪያው ንፈስ ስልክ አቦ መግቢያ እንድትገኙ ኮሚቴው ጥሪውን ከአደራ ጭምር ያስተላልፋል::
የ13ኛ ዙር 20/80 የቤት ባለእድለኞች አብይ ኮሚቴ