Get Mystery Box with random crypto!

ቆቦ በዛሬው እለት በህወሃት ሀይሎች ቁጥጥር ስር ገብታለች መንግስት በበኩሉ መከላከያ የከተማ | ደሴ ታይምስ®️ - ወሎ

ቆቦ በዛሬው እለት በህወሃት ሀይሎች ቁጥጥር ስር ገብታለች

መንግስት በበኩሉ መከላከያ የከተማ ውጊያ ላለማድረግ ከቆቦ ወጥቷል ሲል በ ኮሚውንኬሽኑ አማካኝነት አስታውቋል

አሸባሪው ሕወሐት በአንድ በኩል የተለመደውን የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማ ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል።
የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል።
አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል።

via:Government communication

እያፈገፈግን ነው ተብሎ ማስረከብ?

ደሴ ታይምስ ➤ @DessieCity

ወሎዬ ስራዎች ➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
www.facebook.com/DesieTimes