Get Mystery Box with random crypto!

Appreciation Post እጅግ የምናከብረው የቮልስዋገን አድናቂ እና አፍቃረከ መኪኖቹን ጥንቅ | ድሮም ዘንድሮም ™ 🇪🇹

Appreciation Post

እጅግ የምናከብረው የቮልስዋገን አድናቂ እና አፍቃረከ መኪኖቹን ጥንቅቅ አድርጎ የሚሰራ የሚጠግነው ሳምዲዮ(Samdeo) ወደ አሜሪካ ከሄደ ጀምሮ አካላቸውን በተለያየ መንገድ ላጡ እና የሚረዳ የሚያግዝ ላጡ ወገኖቻችን 'ሞተር ዊልቼር(Motorized Wheelchair' እራሱ ወርክሾፕ ከራሱ ገንዘብ አውጥቶ እየገዛ፣ እየሰራ ወደ ሀገር እንደሚልክ ታውቃላችሁ? ይህንን ጥረቱን አይታችሁ ማገዝ የምትፈልጉ መተባበር ምትፈልጉ፣ ወደ ሀገር ይህንን ዊልቼር ለማጓጓዝ በተለያየ መንገድ ማገዝ ምትፈልጉ በግል ብታወሩት እና ለእንደዚህ አይነት ነገር አትኩሮት ብንሰጥ ብዙ ስራ እናቀላለን።

ሳምዲዬ የስንት እናቶችን እምባ ያበሰ፣ ድካማቸውን ሸክማቸውን፣ ሀሳባቸውን የተካፈለ እና ያቀለለ በጎ ፈቃደኛ ምርጥ ኢትዮጲያዊ ለወገኑ አሳቢ ደራሽ ነው።

በውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያለን ሰዎች የአቅማችንን ማድረግ እንደምንችል ምክንያት ሳናበዛ እንደ ሳምዲዮ መርዳት እንችላለን እና ሳምዲዮ እጅህ ይባረክ፣ የሰራኸው በጎ ተግባር መልሶ ይክፈልህ፣ ወንድማችን በርታ እናመሰግናለን እንበለው።

@deromzenderom