Get Mystery Box with random crypto!

​​ አማላጅ ነው በፍጡራንና ፈጣሪ መካከል ድርሻ የተሰጠው ሰውን ለማገልገል ተራዳኢው መልአክ | የኮ/ቻ ደብረ ሲና ቅ/ሚ ቤ/ን ሰ/ት ቤት

​​ አማላጅ ነው

በፍጡራንና ፈጣሪ መካከል
ድርሻ የተሰጠው ሰውን ለማገልገል
ተራዳኢው መልአክ ጠባቂ የእስራኤል
የመላእክት አለቃ ስሙ ነው ሚካኤል

አማላጅ ነው ሚካኤል(፪)
የአምላክ ባለሟል
ለነሙሴ ለህዝበ እስራኤል

ፈርዖን እንደገና ልቡ ተጸጽቶ
ሲከታተላቸው ጦሩን አስከትቶ
ይመራቸው ጀመር ሚካኤል በፋና
ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና
አዝ = = = = = =
ሙሴ እንደታዘዘው አነሳ በትሩን
እጆቹን ዘረጋ ገሠፀው ባህሩን
እንደ ግንብ ቆመ ባህረ ኤርትራ
በደረቅ አለፉ እስራኤል በተራ
አዝ = = = = = =
በአፎሚያ ላይ ሲፎክር ጠላት
ፈጥነህ የደረስከው ሊቀ መላእክት
እኛንም ጠብቀን ከክፉ መቅሰፍት
ፈጥነህ ድረስልን ሁነን እረዳት
አዝ = = = = = =
መልአኩ ሚካኤል አማላጃችን
እንለምንሃለን እንድትጠብቀን
አምላክ በፍርድ ቀን ጻድቃንን ሲጠራ
ዋስ ጠባቂ ሁነን ሚካኤል አደራ

መልካም በአል
"ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን
ተዋጉ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር
ተዋጋ አልቻላቸውምም"
ራእ፲፪፥፯

@debrecina ይቀላቀሉን