Get Mystery Box with random crypto!

ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ ሞን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ በሰላም አለፍኩ በፀጥታ ሁሉ ተችሎ በአንተ ጌታ(2) | የኮ/ቻ ደብረ ሲና ቅ/ሚ ቤ/ን ሰ/ት ቤት

ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ
ሞን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በፀጥታ
ሁሉ ተችሎ በአንተ ጌታ(2)
………..አዝ……
በአንተስ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅርህ ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኸው በአንተ ሞት
ይሄው አቆምከኝ በህይወት(2)
………..አዝ……
ደጅህ ስጠና ስማፀንህ
መቼ ጨከነ ጌታ ልብህ
እንደ ቀራጩ አጎነበስኩ
ምህረት ፀጋህን ከእጅህ ለበስኩ(2)
………..አዝ……
ዘወትር እልል ብል ብዘምር
ስለገባኝ ነው ያንተ ፍቅር
ጌታ ምጠራው ስምህን
ለውጠኸው ነው ታሪኬን(2)
………..አዝ……
አይኞቼ አያዩ ከአንተ በቀር
የምትወደድ የምትፈቀር
ዘመዴ በወገኔ ሆነኸኛል
እኔን የሚችል የት ይገኛል(2)