Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን

የቴሌግራም ቻናል አርማ deaconmelakuyifru — ቀሲስ መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን
የቴሌግራም ቻናል አርማ deaconmelakuyifru — ቀሲስ መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን
የሰርጥ አድራሻ: @deaconmelakuyifru
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.01K
የሰርጥ መግለጫ

ቀሲስ መልአኩ ይፍሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ቄስ እና የኪነ ሕንጻ ባለሙያ ነው። ይህ የመጦመሪያ ምኅላፍ (channel) ልዩ ልዩ የቅድስት ቤተክርስቲያን ትምህርቶች እና ዝክረ ቅዱሳን ይቀርብበታል።
ለአስተያየት፥
Facebook፤
Melaku Yifru Zewludebirhan
0910657637
@EqubeAbaGiorgis

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-19 22:18:09 Watch "በዓለ ደብረ ታቦር" on YouTube


141 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 12:21:17
(ከቅድስት ማርያም መግደላዊት መልክእ)
+ + +

ሰላም ለቃልኪ ቅድመ ሐዋርያት ዘጸርሐ፣
ምስለ እስትንፋስ ወጒርዔ ኀበ ስቴ ወይን ፍስሐ፣
መግደላዊት ማርያም እንተ ትሠረገዉ ንጽሐ፣
ጽንሕኒ እግዝእትየ እስከ እረክብ ንስሓ፣
እስመ ላእሌየ ኃጢአት በዝኃ።

. . . .

ሰላም ለመዝራዕትኪ እመዝራዕት ልዑላት፣
ወለኲርናዕኪ ክቡድ እምነ ሐጺን ወብርት፣
መግደላዊት ማርያም ቤዛዊተ ጸጋ ወሀብት፣
ሠውርኒ በጽላሎትኪ እም ኲሉ መንሱት፣
ወባልህኒ እምዳግም ሞት።

አምላከ ቅድስት ማርያም መግደላዊት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኃጥእ ባርያዎችህን ስለቅድስት ወዳጅህ ብለህ ማረን ይቅርም በለን።
265 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 11:54:10
155 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, 08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 11:54:10 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በዲያቆን መልአኩ ይፍሩ

የነሐሴ ፯ ዝክረ ቅዱሳን።

እንኳን ለዓለሙ ብርሃን እናት #ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_የጽንሰት ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

¶ አመ ፯ ለነሐሴ በዛቲ እለት፥ ፈነዎ እግዚአብሔር ለገብርኤል ሊቀ መላእክት ኀበ ክቡር ወልዑል ኢያቄም ጻድቅ፣ ወአይድዖ በራእይ #ፅንሰታ_ወልደታ_ለእግዝእትነ_ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ወከመ ይከውን ባቲ ፍሥሓ ወመድኃኒት ለኲሉ ዓለም።

፩-ነሐሴ ፯ በዚህች ዕለት እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው፤ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን #ፅንሰቷንና_ልደቷን በርሷም ለዓለሙ ኹሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው።

+ ይህም ቅዱስ ኢያቄም ከሚስቱ ቅድስት ሐና ጋር ልጅ ስላልነበራቸው እጅጉን ያዝኑ ነበር። በዚህም የተነሳ ( አይድሁድ ልጅ የሌለአ ከእግዚአብሔ የተረገመ ጸጋ በረከት የሌለው ነው ብለው ያምኑ ነበርና) ከአይሁድ ብዙ መገለልንና መከራ ተቀበሉ። በዚህም በተለይም ቅድስት ሐና እናታችን ብዙ ታዝን ነበር። አንድ እለትም ቤተ መቅደስ ደርሳ አልቅሳ ስትመለስ ርግቦች ከገላግልቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ አይታ ከእሊህ ግእዛን ከሌላቸው ፍጡራን እኔን የማንስ ድንጋይ ነኝነ ብላ እጅጉን አለቀሰች። እግዚአብሔርም ቸር ነውና ስዕለታቸውን እና ጸሎታቸውን ሰምቶ ራእይን አሳያቸው፣ እርሱ ለርሷ እርሷም ደግሞ ለርሱ።

+ እርሱም ለርሷ ጸዓዳ ዖፍ ሰማያትን ሰንጥቃ መጥታ በቀኝ ዠሮዋ ገብታ በማኅፀኗ ስታድር፣ እርሷም ደግሞ ኢያቄምን ሲያስታጥቁትና በትሩ ለምልማ አብባ አፍርታ የዓለም ኹሉ ሰው ፍሬዋን ሲመገብ ተመለከቱ። በዚህም እጅግ በመደነቅ ያለቅሱ ነበር። በጥዋትም ያዩትን ተነጋገሩና ከኹሉ በፊት ጸሎት ያዙበት። ኢያቄምም ለጸሎት ለሱባኤ ወጣ ብሎ ከአንድ ተራራማ ቦታ ገባና በዚያ መትጋት ጀመረ። እነርሱም ኹለታቸው ልጅ ቢሰጣቸው ለእግዚአብሔር እንደሚሰጡ ተስለው ነበርና።

+ በዚህም እለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ቅዱስ ኢያቄም መጥቶ የምሥራቹን ነገረውና ከቅድስት ሐና እንዲደርስ ይነግረዋል። ቅዱስ ኢያቄምም የእግዚአብሔርን የቸርነቱን ሥራ እያደነቀ ወደቤቱ ተመልሶ በቸሩ አምላክ ቅዱስ ፈቃድ የዓለም ብርሃን የሆነውን እውነተኛ ፀሐይ የወለደችልንን ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና አልባቲ ሙስና የተባለች ወላዲተ አምላክን በዛሬዋ እለት ተፀነሰችልን። ይህንንም ይዞ ታላቁ ሊቅ አባ ሕርያቆስ "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ - ድንግል ሆይ በኃጢአይ በሚደረግ ሩካቤ የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በኾነ ቅዱስ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ" ይለናል።

+ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

፪-ዳግመኛም በዚህች የሐዋርያት አለቃ #የከበረ_የጴጥሮስ በዓል ነው።

+ በዚህችም እለት ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ቢጠይቃቸው በልባቸው ያለውን ነገር በሌሎች ሰዎች አድርገው ነግረውት ነበር። አስቀድሞም ሐዋርያት (መንፈስ ቅዱስ ገና ስላልተሰጣቸው) ይጠራጠሩ ነበርና ይህነን ነገር ሲጠያየቁ አንዳንዶቹ ኤልያስ ነው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ኤርምያስ ይሆን፣ ሌሎቹም ደግሞ ከነቢያት አንዱ ይሆን? ሲሉ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን እስኪ አቅናለን አንተ ምን ትላለህ ቢሉት፣ ተዉ እርሱስ አምላክ ወልደ አምላክ የኾነ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነው አላቸው።

+ ቸሩ አምላካችንም ይህንን እምነቱን በኹላቸውም ፊት ሊገልጥለት ወደደና በፊልጶስ ቂሣርያ ጠየቃቸው። እነርሳቸውን ያሰቡትን በሌሎች ሰዎች አስመስለው ሲናገሩ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀበል አድርጎ አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ብሎ መሰከረ። ቸሩ አምላካችንም ይህን ደማዊ ሥጋዊ ዕውቀት አልገለጠልህምና ጴጥሮስ ሆይ አንተ አለት ነህ፣ በአንተም አለትነት ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ፣ የሲዖል ደጆችም አይችሏትም፣ ለአንተም የመንግስተ ሰማያትን ቁልፍ እሰጥሃለሁ ብሎታል።

+ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በጌቶቻችን በሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ለሁላችን ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

ሰላም ዕብል ለጴጥሮስ ሥዩም
ላዕለ ሐዋርያት ኄራን ካህናተ ኲሉ ዓለም
ሶበ ለክርስቶስ አምኖ ከመ ወልደ አምላክ ዮም
ኢከሠተ ለከ ይቤሎ ዘሥጋ ወደም
እንበለ አቡየ ዘሀሎ እምቅድመ ዓለም።

፫-ዳግመኛም በዚህች ዕለት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ጢሞቴዎስ አረፈ።

+ ታላቁ ተጋዳይ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮስቆሮስ ካረፈ በኋላ የተሾመ ደገ'ኛ ሊቀ ጳጳስ የነበረ ሲኾን ብዙ መከራን የተቀበለና ገድለኛ አባት ነው። ደጋግመው ከመንበሩ አሳደውት ነበረ፣ መርቅያን የተባለው መናፍቅ ንጉሥ በነገሠ ጊዜ በርሱም ላይ መናፍቅ ጳጳስ ሹሞበት ነበር። መርቅያን ሲሞትም ወደ መንበሩ ተመልሷል። ብዙ መከራን ተቀብሏል። በመርቅያን ልጅ በልዮንም ደግሞ መከራ ስደት ደርሶበታል። ኋላ ግን ዘይኑን ሲነግሥ ዳግመኛ ወደ መንበሩ ተመልሷል። ለሃያ ሁለት ዓመታትም በመንበሩ በበጎ አገልግሎት ሲያገለግል ቆይቶ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

ሰላም ለጢሞቴዎስ እንተ ረሰየ ምርዋጾ
ለምሂር ወለገሥጾ
በመሠረተ ወርቅ ወብሩር ነፍሳተ ብዙኃን ሐኒፆ
ወበእንተ ዘኮነ በስደት ቢጾ
እምዕሴተ ዲዮስቆሮስ አብ ዕሴቱ ኢሐጾ።

፬-ዳግመኛም በዚህች ዕለት የራኄል ልጅ #ዮሴፍ (ወልደ ያዕቆብ) ተወልደ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

፭-ዳግመኛም በዚህች ዕለት እግዚአብሔርን የሚወዱት ታላቁ #የኢትዮጵያ_ንጉሥ_አፄ_ናዖድ ዕረፍታቸው ነው። እኒህም ንጉሥ እመቤታችንን የስምንተኛውን ሺህ ዘመኑን አታሳዪኝ ውኃውንም አታጠጭኝ እያሉ ይማጸኗት ነበር። ቸሩ አምላክም ልመናቸውን ተቀብሎ በ፲፬፻፺፱ ዓ.ም ነሐሴ ፯ በዚህች ቀን ወደ ሰማያዊት መንግስቱ ጠራቸው። ንጉሥም መፍቀሬ ድንግል የኾኑ ሲሆን ድርሳናትንም የደረሱ ደገ'ኛ ንጉሥ ናቸው። መልክአ ማርያም የሚባል ታላቅ ጥዑም ድርሰትም አላቸው። በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በእንተ ቅዱስ ኢያቄም ወቅድስት ሐና ወበእንተ እግዝእተ ኲሉ መድኃኒተ ኲሉ ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም ድንግል በክልኤ እምከ ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለኮነ ተዝካረ በዓሎሙ በይእቲ እለት መሐረነ ለነ ለአበስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ አሜን።

እግዚኦ ተዘከር ኪዳን ዘወሀብኮሙ ለቅዱሳን አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አስመሩ ኪያከ፣ ወሶበ ተዘከርከ ዘንተ ተዘከር ከመ መሬት ንሕነ አባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ፣ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቅድስት ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተ ክርስቲያን። ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት፣ ፍጡነ ይርከበነ ሳህልከ እግዚኦ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
141 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, 08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 11:54:10
86 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, 08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 11:54:10
84 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, 08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 11:54:10 እንኳን ለዓለሙ ብርሃን እናት #ለቅድስት_ማርያም_መግደላዊት እና ለሌሎቹም ክብረ በዓላት በሰላም አደረሳችሁ።

※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※

የነሐሴ ፮ ዝክረ ቅዱሳን።

በዲያቆን መልአኩ ይፍሩ

※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

¶ አመ ፮ ለነሐሴ በዛቲ እለት፥ ኮነት ሰማዕተ #ቅድስት_ኢየሉጣ_ዘምሀገረ_ቂሳርያ_ወቀጰዶያ።

፩-ነሐሴ ፮ በዚህች ዕለት #ከቂሳርያ እና #ከቀጰዶቅያ_አገር የከበረች #ኢየሉጣ ምስክር ሁና ሞተች።

+ ይህችንም ቅድስት አንድ ዐመፀኛ ሰው ገንዘቧን ኹሉ በግፍ ዳኛ ወሰደባት። ኋላም እንደምትከሰውና ሐሰቱንም ልትገልጥበት እንደምትችል ሲያውቅ ክርስቲያን መኾኗን ገልጦ በቂሳርያው ገዥ ዘንድ ወነጀላት። እርስዋም በልቧ እንዲህ ያለ'ውን ምድራዊ ገንዘብ ሰዎች የሚጥቁኝ ኃላፊ ጠፊ ኹኖ ሳለ አይደለምን? እንግዲህስ የማይነጥቁኝን ሰማያዊ ሀብት ገንዘብ ማድረግ አለብኝ ብላ አሰበች።

+ ወደ ንጉሡም ቀርባ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነች። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጥቶ ከእሳት ውስጥ አስጣላት፣ እሳቱ ምንም ምን ሳይነካት ነፍሷን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች። ከእሳቱም ልክ ከውሃ እንደሚወጣ አወጧት። ቅዱስ ባስልዮስም ስለርሷ ብዙ ተናግሮ አመስግኗታል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

፨፨፨አርኬ፨፨፨
ሰላም ለኢየሉጣ እንበይነ ምግባራ ሠናይ
በውስተ እቶን ዘአብእዋ በውዴተ ብእሲ እኩይ
እንዘ ኢሀሎ ላዕሌሃ አሠረ ዋዕይ
ወጽአት እምእሳት ከመ ዘወጽአ እማይ
አምሳለ ፍቱን ወርቅ ወብሩር ጽሩይ።

፪-ዳግመኛም በዚህች ዕለት የአባ ሲኖዳ ረድእ #ቅዱስ_አባ_ዊፃ አረፈ።

+ ይህም ቅዱስ ከእግዚአብሔር ብዙ ምስጢራትን የሰማና የአባ ሲኖዳንም ገድል እንደአየና እንደሰማ የጻፈ ነው። መልካም አካሔዱንም እንዴት እንደፈጸመ ከእርሱ ከአባ ሲኖዳ ሰማ፣ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። እግዚአብሔር በጸሎቱ ይማረን አሜን።

፫-ዳግመኛም በዚህች ዕለት ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የከበረች #ማርያም_መግደላዊት አረፈች።

+ ከዚህም በኋላ ጌታችንን ተከትላ አገለገለችው። በመከራውም ስንኳን ጊዜ ፈጽሞ አልተለየችም። እርሱም በተነሳበት እለት ወደ መቃብሩ ገሥግሣ ተመልክታ ባጣችው ጊዜ ከኋላዋ ተገለጠላትና አፈ ወርቅ ዮሐንስ እንደሚናገረው የሚያነጋግሯት መላእክት እጅ ሲነሱት ተመልክታ ዘወር ብትል አየችው። አላወቀችውምና አትክልተኛም መስሏት ነበርና የጌታዬን ሥጋ አንተ ወስደኸው እንደኾነ ብላ ጠየቀችው። እርሱ ግን በስሟ ጠራት ያን ጊዜም አወቀችው።

+ ስለመጠራጠሯና ስለብዙ ምክንያት እንዳትነካው ከገሠጻት በኋላ ከሞት መነሳቱንና የማረጉን ነገር ለደቀ መዛሙርት እንድትነግር የታደለች ደገ'ኛ እናት አደረጋት። ከዕርገቱም በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያትን ብዙ እያገለገለች ኖረች። ወንጌልንም ሰብካ ብዙዎችን ወደ ቀናችው ጎዳና መለሰች። ስለዚህም ግብሯ ደግሞ ስለማስተማርም ትተጋ ዘንድ ቅዱሳን ሐዋርያት ዲያቆናዊት አደገው ሾሟት። ከአይሁድም በመገረፍና በመጎሳቈል ብዙ መከራን ተቀበለች። በጐ አገልግሎቷንም ፈጽማ በሰላምአረፈች። ለእግዚአብሔር ማስጋና ይሁን፣ እኛንም የክርስቲያን ወገኖችን ኹሉ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

፨፨፨አርኬ፨፨፨
ሰላም ለመግደላዊት ማርያም ስማ
ለኢየሱስ ዘርእየቶ እምሐዋርያት ቀዲማ
ወለእንስት ሰላም ዘተሳተፋ ድካማ
እንዘ ይትራወጻ ኀበ መቃብሩ ለፌማ
እንበለ ያፍርሆን ዘሌሊት ግርማ።

፨፨፨ጸሎት፨፨፨
ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በእንተ ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕት ቂሳርያ ወቆጵሮስ ወቅድስት ማርያም መግደላዊት ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለኮነ ተዝካረ በዓሎሙ በይእቲ እለት መሐረነ ለነ ለአበስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ አሜን።

እግዚኦ ተዘከር ኪዳን ዘወሀብኮሙ ለቅዱሳን አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አስመሩ ኪያከ፣ ወሶበ ተዘከርከ ዘንተ ተዘከር ከመ መሬት ንሕነ አባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ፣ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቅድስት ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተ ክርስቲያን። ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት፣ ፍጡነ ይርከበነ ሳህልከ እግዚኦ።

※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※

የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ስለ ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕተ ቂሳርያ ወቆጵሮስ እና ስለ ቅድስት ማርያም መግደላዊት ብለህ፣ በዚህችም እለት ዝክረ በዓላቸው ስለ ኾነ ስለ ሌሎቹም ኹሉ ቅዱሳን ብለህ እኛን በደለኛ የወንድና የሴት አገልጋዮችህን ማረን።

ጌታ ሆይ አንተን ደስ ላሰኙህ ቅዱሳን የገባህላቸውን ቃልኪዳን አስብ፣ ይህንም ባሰብህ ጊዜ ደግሞ እኛ በደለኞች የሴትና የወንድ አገልጋዮችህ አፈር ትቢያ መኾናችንን አስብ፣ የቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያን እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ፈጽሞ አታሳየን። የቀደመውን (በደላችንን) አስበህብን አታጥፋብ፣ አቤቱ ምሕረትህ ፈጥኖ ያግኘን እንጂ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

በቴሌግራም፥ @deaconmelakuyifru
በዩቲዩብ፥ https://www.youtube.com/channel/UCP-sKuhsHg_4HrWtcJx2r8Q

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
141 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, edited  08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:57:07 እንኳን ለሰማዕታት #እንድራኒቆስ #ወአትንናስያ፣ ለአበው ቅዱሳን #አብርሃም #ይስሐቅ #ወያዕቆብም ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※

የሐምሌ ፳፰ ዝክረ ቅዱሳን።

በዲያቆን መልአኩ ይፍሩ

※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

¶ አመ ፳፰ ለሐምሌ በዛቲ እለት፥ ተዝካሮሙ #ለእንድራኒቆስ ወለብእሲቱ #አትናስያ መፍቀርያነ ክርስቶስ።

፩-ሐምሌ ፳፰ በዚህች ዕለት ክርስቶስን የሚወዱ #የእንድራኒቆስና የሚስቱ #የአትናስያ መታሰቢያቸው ነው።

+ እሊህም ቅዱሳን በአንጾኪያ ከተማ የሚኖሩ ምጽዋትንና በጎ ምግባር የሚወዱ ደጋግ የኾኑ ባለጸጋ ባልና ሚስት ሲኾኑ ቸሩ አምላክ አንድ ወንድና አንድ ሴት ልጅ ሰጣቸው። የወንዱን ስም ዮሐንስ የሴቷን ማርያም ብለው አወጡላቸው። ዐሥራ ኹለት ዓመትም በኾናቸው ጊዜ የሆድ ዝማ በሽታ ያዛቸውና ታመው በአንዲት ቀን ተከታትለው ሞቱ። በዚህም ጊዜ ቅዱስ እንድራኒቆስ ልክ እንደ ጻድቅ ኢዮብ "እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ ስሙ የተመሰገነ ይሁን" ብሎ በአኰቴት ተቀበለው።

+ እናታቸው ቅድስት አትናስያ ግን መሪር ኀዘንን አዘነች። ከኀዘኗም ብዛት የተነሳ በቤተክርስቲያን ሳለች እንቅልፍ ወሰዳትና እንደመነኰስ የመሰለ ተገለጠላትና "በልጆችሽ ሞት አታልቅሺ፣ እነርሱ ግን በሰማያት ደስ እያላቸው ናቸው።" አላት። ይህንም ያየችውን ሰላምታ ለባልዋ ነገረችው። ከዚያም ዓለምን ለመተው ተስማሙና ገንዘባቸውን ኹሉ መጽውተው ወደ በረሃ ወጡ። ሚስቱን በእስክንድርያ ትቷት ከአባ ዳንኤል ዘንድ ከመነኰሰ በኋላ ወስዶ በሴቶች ገዳም አኖራት።

+ እንድራኒቆስም አባ ዳንኤልን አስፈቅዶ ከቅዱሳት መካናት ኢየሩሳሌም ኺዶ ይባረክ ዘንድ ለመኼድ ሲነሳ ሚስቱ አትናስያም ወንድ መስላ አብራው ነበረች። እርሷ አውቃዋለች እንጂ እርሱ ግን አላወቃትም። እርሷም ማንነቷን አልገለጠችለትም። ከዚያም ሲመለሱ አባ ዳንኤል አብረው መኼዳቸውን በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ከዚያ መነኰስ ጋራ አብረው በአንድ እንዲኖሩና እንዲጋደሉ ለእንድራኒቆስ ነገረው። ከዚያም ዐሥራ ኹለት ዓመት አብረው ኖሩ፣ ማንም ግን አላወቀም ነበር። አባ ዳንኤልም ይጎበኛቸውን ስለነፍሳቸውም ጥቅም ያስተምራቸው ነበር። በኋላም ያ መነኰስ በጽኑዕ ታመመና አባ ዳንኤል ይጠራለት ዘንድ ለእንድራኒቆስ ነገረው። ኼዶም ቢጠራውና ቢመጣ ለሞት ደርሶ አገኘው።

+ ሥጋ ወደሙንም ካቀበለው በኋላ ዐረፈ። በሚገንዙትም ጊዜ ሴት መኾኑ ታወቀ። ይህንም ጊዜ ለእንድራኒቆስ ያስቀመጠችውን ማስታወሻና ታሪኳንም ኹሉ አገኙ፣ እንድራኒቆስም ይህን ሲያውቅ ደንግጦ ልቡ ተሠወረ፣ ፊቱንም እየጸፋ ፈጽሞ አለቀሰ። ከዚያም ከጥቂት ቀናት በኋላ ታሞ አረጋውያን መጥተው በረከቱን ተቀብለው ሥጋ ወደሙን ተቀበለና በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በቅዱሳን ኹሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

ሰላም ለእንድራኒቆስ ለምኔተ አስቄጥስ ዘሐወጻ
እንዘ ይዘሩ ብዕሎ ዘኢኮነ ብዕለ አመፃ
ወለአትናስያ ሰላም ለነቢር ዘተባየጻ
ከመ ይእቲ ብእሲቱ እንበለ ይጠይቅ ገጻ
እስመ አዕፅምቲሃ በጽምእ ከመ ሣዕር ነቅጻ።

፪-ዳግመኛም በዚህች ዕለት የጋግ መፍቀርያነ እግዚአብሔር አበው #የአብርሃም #የይስሐቅና #የያዕቆብ መታሰቢያቸው ነው።

፨፨፨ጸሎት፨፨፨
ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በእንተ ቅዱሳን እንድራኒቆስ ወአትናስያ ወበእንተ ቅዱሳን ኅሩያን አበው አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ኲሎሙ ቅዱሳን እለኮነ ተዝካረ በዓሎሙ በይእቲ እለት መሐረነ ለነ ለአበስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ አሜን።

እግዚኦ ተዘከር ኪዳን ዘወሀብኮሙ ለቅዱሳን አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አስመሩ ኪያከ፣ ወሶበ ተዘከርከ ዘንተ ተዘከር ከመ መሬት ንሕነ አባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ፣ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቅድስት ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተ ክርስቲያን። ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት፣ ፍጡነ ይርከበነ ሳህልከ እግዚኦ።

※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※

የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ስለ ቅዱሳን እንድራኒቆስና ርትናስያ፣ ስለተመረጡ ቅዱሳን አባቶች አብርሃም ይስሐቅ እና ያዕቆብ ብለህ፣ በዚህችም እለት ዝክረ በዓላቸው ስለ ኾነ ስለ ሌሎቹም ኹሉ ቅዱሳን ብለህ እኛን በደለኛ የወንድና የሴት አገልጋዮችህን ማረን።

ጌታ ሆይ አንተን ደስ ላሰኙህ ቅዱሳን የገባህላቸውን ቃልኪዳን አስብ፣ ይህንም ባሰብህ ጊዜ ደግሞ እኛ በደለኞች የሴትና የወንድ አገልጋዮችህ አፈር ትቢያ መኾናችንን አስብ፣ የቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያን እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ፈጽሞ አታሳየን። የቀደመውን (በደላችንን) አስበህብን አታጥፋብ፣ አቤቱ ምሕረትህ ፈጥኖ ያግኘን እንጂ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

በቴሌግራም፥ @deaconmelakuyifru
በዩቲዩብ፥ https://www.youtube.com/channel/UCP-sKuhsHg_4HrWtcJx2r8Q

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
257 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:57:04
159 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 08:47:15 ፨፨፨ጸሎት፨፨፨
ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በእንተ ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት ወበእንተ ቅዱሳን ሰማዕታት ማኅበራኒሁ ለአባ ኖብ ወበእንተ ቅዱስ ስምዖን ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለኮነ ተዝካረ በዓሎሙ በይእቲ እለት መሐረነ ለነ ለአበስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ አሜን።

እግዚኦ ተዘከር ኪዳን ዘወሀብኮሙ ለቅዱሳን አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አስመሩ ኪያከ፣ ወሶበ ተዘከርከ ዘንተ ተዘከር ከመ መሬት ንሕነ አባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ፣ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቅድስት ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተ ክርስቲያን። ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት፣ ፍጡነ ይርከበነ ሳህልከ እግዚኦ።

※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※

የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ስለ ቅዱስ ሰማዕት አባ ኖብ እና ስለ ማኅበርተኞቹ ቅዱሳን ሰማዕታት፣ ስለ ቅዱስ ስምዖን ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ ብለህ፣ በዚህችም እለት ዝክረ በዓላቸው ስለ ኾነ ስለ ሌሎቹም ኹሉ ቅዱሳን ብለህ እኛን በደለኛ የወንድና የሴት አገልጋዮችህን ማረን።

ጌታ ሆይ አንተን ደስ ላሰኙህ ቅዱሳን የገባህላቸውን ቃልኪዳን አስብ፣ ይህንም ባሰብህ ጊዜ ደግሞ እኛ በደለኞች የሴትና የወንድ አገልጋዮችህ አፈር ትቢያ መኾናችንን አስብ፣ የቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያን እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ፈጽሞ አታሳየን። የቀደመውን (በደላችንን) አስበህብን አታጥፋብ፣ አቤቱ ምሕረትህ ፈጥኖ ያግኘን እንጂ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

በቴሌግራም፥ @deaconmelakuyifru
በዩቲዩብ፥ https://www.youtube.com/channel/UCP-sKuhsHg_4HrWtcJx2r8Q

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
272 viewsDeacon Melaku Yifru Zewlude Birhan ዲያቆን መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን, 05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ