Get Mystery Box with random crypto!

Dire-Dawa University

የቴሌግራም ቻናል አርማ dduniv — Dire-Dawa University D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dduniv — Dire-Dawa University
የሰርጥ አድራሻ: @dduniv
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.79K
የሰርጥ መግለጫ

An Official Channel of Dire-Dawa University

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

3

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 10:04:14
197 viewsSent, 07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 10:04:12
205 viewsSent, 07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 10:04:05 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድዔታ ክቡር ሳሙኤል ክፍሌ ጨምሮ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።
204 viewsSent, 07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:29:41 የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል በ2014 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም እና የ2015 በጀት አመት እቅድ  ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዩኒቨርሲቲው በተጠናቀቀው በጀት አመት በተቀመጡት ስትራቴጂክ ግቦች፣ የፕሮጀክት አፈፃፀም ፣ በበጀት አመቱ ባጋጠሙ ችግሮች እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በመማር ማስተማሩ ዘርፍ ዩኒቨርሲቲውን ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት ለማሻገር የሚያስችሉ ስራዎች መጀመራቸው እና የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አንፃር በ2015 ዓ.ም ለመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች ሊሰጥ የታቀደው የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ዝግጅት መጀመሩን በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይም በምርምርና ማኅበረሰብ አገልግልት በበጀት ዓመቱ በርካታ ውጤታማ ስራዎች የተሰሩ መሆናቸውን፣ በመሠረተ ልማት ማሳፋፋት ስራዎች ዘርፍም በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ክንውናቸው በሪፖርት ላይ ተገልጿል፡፡

በግምገማዊ መድረኩ ዩኒቨርሲቲው በ2014 ዓ.ም በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማኅበረሰብ አገልግልት እንዲሁም በመሠረተ ልማት ግንባታ እና ማስፋፊያ ስራዎች ላይ ከእቅዱ አንፃር በበጀት ዓመቱ የነበረው አፈፃፀም በዝርዝር ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመድረኩ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የዩኒቨርሰቲ ካውንስል አባላት በቀረበው ሪፖርት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን በማቅረብ ውይይት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው በ2015 በጀት ዓመት ሪዕይና ተልዕኮውን እንዲሳካ እና የተጀመሩት የለውጥ ስራዎች ከግብ እንዲደርሱ ማህበረሰቡ ሁሉም በየ ደረጃው ለእቅዱ ተፈፃሚነት ሀላፊነቱን እና ግዴታው በተሻለ ሁኔታ እንዲወጣ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በንግግራቸው አሳስበዋል።

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: https://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw
1.6K viewsSent, 19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:29:37
1.5K viewsSent, 19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:59:43 በሀገራችን አዲስ የተከሰተችውን አኖፕለስ ስቴፈንሲ የተሰኘች የወባ በሽታን አምጪ ትንኝ መከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ዛሬ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አኖፕለስ ስቴፈንሲ (Anopheles Stephensi) የተሰኘችው የወባ በሽታ አምጪ ትንኝ በቅርቡ በአስተዳደራችችን ድሬደዋን ጨምሮ በሶማሌ ፣ በአፋር እና በተወሰኑ የኦሮምያ ክልል ከተሞች መከሰቷ ተረጋግጧል፡፡

ይህቺን በሀገራችን እንደ አዲስ የተከሰተች የወባ በሽታን አምጪ ትንኝ በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት ከማድረሷ በፊት አስቀድሞ ለመከላከል በአሜሪካ መንግስት ( U.S. President's Malaria Initiative vectorlink Ethiopia) በተደረገ የገንዘብ ድጋፍ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የታቀፉበት ፕሮጀክት በዛሬው እለት በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በይፋ የፖሮጀክቱ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

በዚሁ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የድሬደዋ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘር ኃላፊ የተከበሩ አቶ ኢብራሒም ዩሱፍ ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢንባሲ ትሬሲ ጃኮብሰን ፣ የድሬደዋ አስተዳዳር ጤና ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ፣ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ይህንኑ የፖሮጀክት ማብሰሪ ፕሮግራም በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ዩኒቨርሲቲው በምስራቁ አካባቢ ያለው የጤና አገልግልት እንዲሻሻል የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ በቅርቡ በድሬደዋና በአካባቢው እንደተከሰተች የተረጋገጠውን አኖፕለስ ስቴፈንሲ (Anopheles Stephensi) የተሰኘችውን የወባ በሽታን አምጪ ትንኝ በማኅበረሰባች ላይ ጉዳት ከማድረሷ በፊት አስቀድሞ ለመከላከል ዛሬ በይፋ የተጀመረው ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በትንኝ ንክሻ የሚተላለፉ በሽታዎች የአስተዳደራችንን ዋነኛ የማኅበረሰባችን የጤና ችግሮች መሆኑን የገለጹት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር እነዚህን በሽቶች ለመከላከልና ለመቆጣጠር በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰው በተለይም የአስተዳደሩ ከፍተኛ የካቢኔ አባላትና ከፍተኛ አመራሮች የሚሳተፉበት የእለተ ቅዳሜ የፅዳት ፕሮግራም ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አስተዳዳር በዚህ ፕሮጀክት ላይ በቀጥታ ተሳትፎ ያላቸው የአሜሪካ መንግስት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር፣ የድሬደዋ ጤና ቢሮ እና የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ትንኟን ለመከላከል የተከተሉት አዲስ ስልት ሊበረታታ የሚገባውና ሊያስመሰግናቸው የሚገባ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢንባሲ ትሬሲ ጃኮብሰን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ወባን ለማጥፋት የምታደርገውን እንቅስቃሴ አሜሪካ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች ፡፡ በተለይ በአዲስ መልክ በኢትዮጵያ የተለያዩ የክልል ከተሞች የተከሰተችውን አኖፕለስ ስቴፈንሲ የተሰኘችውን የወባ በሽታ አምጪ ለማጥፋት ለሚደረገው ጥረት ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የድሬደዋ አስተዳዳር ጤና ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ካለፈው ዓመት ወዲ በአስተዳደሩ በትንኝ ንክሻ አማካኝነት ከወባ በሽታ በተጨማሪ የደንጊ ትኩሳትና የቺኩንጉኒያ በሽታዎች በማኅበረሰባች ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር እያስከተሉ እንደሚገኙ ጠቅሰው በተለይ ካለፈው ዓመት ወዲህ የነዚ ወረርሽኝ ሽረጭት መጨመር ተከትሎ ከዚህ ቀደም የወባ በሽታን በመከላከል ረገድ ያስመዘገብነው ውጤትን በዘላቂነት ማስቀጠል እንዳንችል ከባድ ፈተና እየፈጠረብን በመሆኑ ሁላችንም ተረባርብን ፖሮጀክቱን ስኬታማ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አንደ ድሬደዋም የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ፣ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው እልት የፕሮጀክት መጀመር ማብሰሪያ ፕሮግራም መካሄዱ ተነግሯል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: https://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw
1.3K viewsSent, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:59:32
1.2K viewsSent, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:59:31
1.1K viewsSent, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ