Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊም ሆኖ የሙስሊሙ ተቋም ስለሆነው የመጅሊስ ጉዳይ ሳያሳስበው የሚቀር አለ ብዪ አልገምትም ። ሆ | የአቡ ሱለይማን ዳውድ ያሲን የመማማሪያ መድረክ

ሙስሊም ሆኖ የሙስሊሙ ተቋም ስለሆነው የመጅሊስ ጉዳይ ሳያሳስበው የሚቀር አለ ብዪ አልገምትም ። ሆኖም ግን ሁሉም ግለሰብ በመጅሊስ ጉዳይ መናገር ፣ መፃፍ አለበት ምንም ያልተነፈሰ ከሆነ ችግር አለበት ብሎ ማሰብ የጤንነት አይመስለኝም ። ብዙ ግለሰቦች ስለ መጅሊስ መስተካከል እየለፉ ፣ እየተጨነቁ ፣ ዱአ እያደረጉ ነገር ግን ከፊት ለፊት ላታያቸው ትችላለህ ። እነ እከሌ ተገኙ እነ እከሌ አልተገኙም ከሚል አጉል ምልከታ ይልቅ ምን ነበር ያጣነው አሁንስ ምን አገኘን ወይም ምን ማግኘት አለብን የሚለው ላይ ትኩረት ማድረጉ ተገቢ ነው ። ጉዳዮ ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም እንዳይሆን ጉዳያችን እና ስራ ላይ ትኩረት እንዲደረግ ግለሰቦችን መስቀልልና ማውረድ ቀርቶ ክፍተቶቻችን ላይ መመካከር ከአዲሱ የመጅሊስ አመራሮች ምን ይጠበቃል በሚለው ዙሪያ አቅሙ ያለው ሰው ትኩረት ቢያደርግበት መልካም ነው ።
በተረፈ አሁን የተገኘው ለውጥ በትክክል መሬት ላይ ወርዶ ለዘመናት እየተንከባለለ የመጣውን ብልሹ አሰራር አስተካክሎ ከፌዴራል እስከ መሳጅድ ድረስ ያለውን መዋቅር አስተካክሎ ህብረተሰቡ ቁርአንና ሀዲስን ሰሀባዎች በተረዱበት ግንዛቤ እንዲገነዘብ ፣ እንዲሁም የሙስሊሙን መብት በማስከበር ሂደት ላይ ቅድሚያ ተሰላፊ ሆኖ ማስፈፀም ሲችል ነው ።
ፈጣሪያችን አላሁ ተአላ መሪዎችንም ተመሪዎችንም ለመልካም ነገር ያግራን ።
T.me/dawudyassin