Get Mystery Box with random crypto!

ሁሌም የውስጥ ሰላምህን ጠብቅ 'አንድ ሰው በራሱ ጉዳይ ተረብሾ መጥቶ ቢለክፍህና አሉታዊ በሆነ መ | 𝐃𝐀𝐖𝐈𝐓 𝐃𝐑𝐄𝐀𝐌𝐒 𝐌𝐨𝐭𝐢𝐯𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐕𝐢𝐝𝐞𝐨𝐬 Ⓜ️

ሁሌም የውስጥ ሰላምህን ጠብቅ

"አንድ ሰው በራሱ ጉዳይ ተረብሾ መጥቶ ቢለክፍህና አሉታዊ በሆነ መንገድ ቢናገርህ እራስህን መቆጣጠር እንጂ መናደድ የለብህም፤ የመጣው ሰው ሁሉ እንዲያናድድህ፤ የመጣው ሰው ሁሉ እንዲያቃጥልህ፤ የመጣው ሰው ሁሉ እንዲያሳብድህ በፍፁም አትፍቀድ፤ አንተ የትልቅ ሕልም ባለቤት ነህ፤ እንዴት የትልቅ ሕልም ባለቤት የሆነ ሰው የውስጡ ሰላም እንዲረበሽ ይፈቅዳል? የራስህን ሰላም ሌላ ሰው በሚያደርገው ድርጊት በመናደድና ምላሽ በመስጠት የምትለወጥ ከሆነ፤ የደስታህን ቁልፍ ለሌላ ሰው በፈቃድህ ሰጥተሃል ማለት ነው፤ ስለዚህ የሰላምህ በር ቁልፉ ምንግዜም በራስህ እጅ ብቻ ይሁን"

ዳዊት ድሪምስ
የሰላም ቀን ተመኘን


በስልጠናዎቻችን ለመሳተፍና የበለጠ መረጃ ለማግኘት በ+251938252525 ይደውሉ።