Get Mystery Box with random crypto!

ዳሸን ባንክ ስፓንሰር ያደረገው ለባዊ ኢንተርናሽናል  አካዳሚ ፓን አፍሪካኒዝም ባዛር  በዛሬው ዕለ | Dashen Bank

ዳሸን ባንክ ስፓንሰር ያደረገው ለባዊ ኢንተርናሽናል  አካዳሚ ፓን አፍሪካኒዝም ባዛር  በዛሬው ዕለት ተከፈተ    

የባዛሩ ብቸኛ የባንክ አጋር የሆነው ዳሸን ባንክ  በባዛሩ ላይ የባንክ  አገልግሎቶቹን  እየሰጠ ይገኛል። 

የለባዊ ኢንተርናሽናል አካዳሚ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ፕሮፌሰር   ፓኖስ ሃትዘያንድሪያስ "ዳሸን ባንክ የባዛሩ ዋና አጋር በመሆኑ እናመሰግናለን" ብለዋል።             

ዳሸን ባንክ ከዚህ ሁነት ባሻገር የለባዊ ኢንተርናሽናል አካዳሚ አጋር መሆኑን ያነሱት ስራ አስኪያጁ የትምህርት ቤቱ የፋይናንስ እንቅስቃሴ በዳሸን ባንክ በኩል እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል። 

ለባዊ ኢንተርናሽ አካዳሚ የዳሸን ባንክ ኮርፓሬት ደንበኛ መሆኑን የጠቆሙት ፕሮፌሰር ፓኖስ ባንኩ ዛሬ በይፋ ለተከፈተው ባዛር እና በቀጣይ ለሚከናወኑ ሁነቶች ከፍተኛ ድጋፍ በማድረጉ አካዳሚው ልባዊ ምስጋና ያቀርባልም ብለዋል።          
 
በባዛሩ ላይ የተሳተፉ ወላጆች ባዛሩ የእርስ በርስ ትውውቅን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ተናግረዋል። በተጨማሪም የትምህርት አጋዥ መጻሕፍትና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለመሸመት ባዛሩ ምቹ አጋጣሚ ፈጥሮልናል ብለዋል።      

በባዛሩ  ላይ የትምህርት አጋዥ መጻሕፍት ፣ ባህላዊና ዘመናዊ አልባሳት ፣ጌጣጌጦችና የሰጦታ እቃዎች ለሽያጭ ቀርበዋል። 

ዛሬን ጨምሮ ባዛሩ ለሁለት ቀናት ለተሳታፊዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።