Get Mystery Box with random crypto!

ዳሽን ባንክ 18 ቢሊዮን ብር ገቢ አስመዘገበ ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት አመት ብር 18 ቢሊዮን | Dashen Bank

ዳሽን ባንክ 18 ቢሊዮን ብር ገቢ አስመዘገበ

ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት አመት ብር 18 ቢሊዮን ገቢ አስመዘገበ፡፡ የባንኩ ባለአክስዮኖች 30ኛ መደበኛ ጉባኤ በስካይላይት ሆቴል ዛሬ የተካሔደ ሲሆን ያለፈው አመት የባንኩ የስራ አፈጻጸም ፣ የዚህ በጀት አመት እቅድና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎባችዋል፡፡

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ያለፈው በጀት አመት በባንክ ኢንዱስትሪው አዎንታዊና አሉታዊ ሁኔታዎቸን የፈጠሩ አለም አቀፋዊና አገራዊ ክስተቶች እንደነበሩ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ዱላ ባለፈው በጀት አመት በኢትዮጵያ የነበረው ማህበራዊና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዲሁም ኢሚዛናዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ የበኩሉን ተጽእኖ ማሳደሩን አስገንዝበዋል፡፡
ምንም እንኳን  የተለያዩ ተግዳሮቶች የነበሩበት አመት ቢሆንም ዳሸን ባንክ ባለፋ በጀት አመት በበርካታ ዘርፎች ውጤታማ እንደነበር አቶ ዱላ ገልጸዋል፡፡ ባንኩ ተጨማሪ 23.6 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ የቻለ ሲሆን አጠቃላይ ሀብቱን 144.6 ቢሊዮን ብር ማድረስ ተችሏል፡፡

ባንኩ በአመቱ የ18 ቢሊዮን ብር ገቢ አስመዝግቧል፡፡ ከትርፍ አኳያ ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት አመት ከግብር በፊት 5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም ከቀደመው አመት ጋር ሲነጻጸር የ31.9 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

የባንኩ የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ የትግበራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎም በቀጣይ አምስት አመታት ተግባራዊ የሚሆን አዲስ ስትራቴጅክ እቅድ መዘጋጀቱን ይህ እቅድ የደንበኞች አገልግሎት በማሻሻል ፣ አገልግሎትን ይበልጥ በማዘመንና የባንኩን ቀጣይ እድገት ላይ እንደሚያተኩር አመልክተዋል፡፡