Get Mystery Box with random crypto!

ሦስቱ የጀሀነም ሸለቆዎች ከነርሱ እንጠንቀቅ!!! ገይ ( ﺍﻟﻐَّﻲ) ወይል ( ﺍﻟﻮ | ❥ ዳሩል ኢስላም/Darul Islam ❥

ሦስቱ የጀሀነም ሸለቆዎች
ከነርሱ እንጠንቀቅ!!!

ገይ ( ﺍﻟﻐَّﻲ)

ወይል ( ﺍﻟﻮَّﻳﻞ)

ሰቀር (ﺳﻘﺮ )
       ሲብራሩ፧

    የገይ ሸለቆ
ሁሉንም ሶላቶች በአንድ ሰብስቦ ለሚሰግድ የተዘጋጀ ሸለቆ ነው።
۞ ﻓَﺨَﻠَﻒَ ﻣِﻦ ﺑَﻌْﺪِﻫِﻢْ ﺧَﻠْﻒٌ ﺃَﺿَﺎﻋُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓَ ﻭَﺍﺗَّﺒَﻌُﻮﺍ ﺍﻟﺸَّﻬَﻮَﺍﺕِ ۖ ﻓَﺴَﻮْﻑَ ﻳَﻠْﻘَﻮْﻥَ ﻏَﻴًّﺎ
(ሱርቱ መርየም፣ - 59)
ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች
ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡

  ወይል
ሸሪዓ ባልፈቀደው ምክኒያት ሶላትን ለሚያዘገዩ ሰዎች የተደገሰች ናት።
ﻓَﻮَﻳْﻞٌ ﻟِّﻠْﻤُﺼَﻠِّﻴﻦَ
(ሱረቱ አል-ማዑን - 4)
ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡
ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻫُﻢْ ﻋَﻦ ﺻَﻠَﺎﺗِﻬِﻢْ ﺳَﺎﻫُﻮﻥَ
(ሱረቱ አል-ማዑን - 5)
ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡

  ሰቀር
ሰቀር ደግሞ ሶላትን ለሚተው ሰው ነው የተሰናዳችው።

ይሄ የእሳት ሸለቆ በጣም ከማቃጠሉ የተነሳ አጥንትን የሚጨርስ ነው።

  ሶላት

የሚተው ሰው ከነፊርዐውንና ሃማን ጋር ነው የሚቀሰቀሰው። የነቢዩን (ﷺ )
ሸፈዓም አያገኝም።


አላህ ሆይ! ሙስሊሞች(ለአንተ ታዛዦች) አድርገህ ግደለን። ከደጋጎች ጎራም
መድበን!
ያረብ አንትው ጠብቀን አሚን

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal