ምክር ከጥበበኛው ሉቅማን ለልጁ ልጄ_ሆይ ፧ በዝምታየ ተፀፅቼ አላውቅም ፡፡ ልጄ_ሆይ ፧ ከጠጣህበት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ድንጋይ አታስገባ፡ ልጄ_ሆይ ፧ ምላስክን ‘አላህ ሆይ ማለትን አለማምድ ለአላህ ጠያቂን የማይመልስበት ሰዓታትአሉትና፡፡ ልጄ_ሆይ፧ ከሌላ ሰው እጅ ካለ በሬ በእጅህ ያለች ወፍ ትበልጣለች ፡፡ ልጄ_ሆይ ፧ ከመገረም ጋር አትሳቅ ከማይመለከትህም ነገር አትጠይቅ፡፡ ልጄ_ሆይ ፧ ሁለት ነገሮችን አታውሳ ፧ ሰዎች ወዳንተ ያደረጉትን በደልና ፣ ለሰዎች ያደረከውን መልካም ነገር፡፡ ልጄ_ሆይ ፧ በጣም ጣፋጭ አትሁን ከንቀት እንዳትበላ መራራ አትሁን እንዳትተፋ ፡፡ ልጄ_ሆይ ፧ ከጥጋብ ላይ ጥጋብ ሆነህ አትመገብ ከምትመገበው ለውሻ ብጥለው የተሻለ ነው ፡፡ ልጄ_ሆይ ፧ የአላህን ፈራቻ ንግድ አድርገህ ያዘው ; ትንሽ የማይባል ትርፋማ ሆኖ ይመጣልሀል፡ @Darul_Islam_channal @Darul_Islam_channal 1.2K views09:58