Get Mystery Box with random crypto!

የሆነ ፖስት ለዚህ ያክል ሰው ተላክ እሄን ያክል አጅር ታገኛለህ ማለት ብይኑ ምንድነው?! መልሱን | Daru Sunnah || ዳሩ ሱን'ናህ

የሆነ ፖስት ለዚህ ያክል ሰው ተላክ እሄን ያክል አጅር ታገኛለህ ማለት ብይኑ ምንድነው?!
መልሱን ከሸይኽ ፈውዛን -ሐፊዞሁሏህ-

ጥያቄ:-
አንዳድ በሰልክ መልእክቶች "በነቢዩ ላይ ሰለዋት አውርዱ ለምሳሌ ለአስር ሰው አስተላልፍ እሄን ያክል አጅር ታገኛለህ" የሚሉ ሰዎች አሉ የዚህ ብይኑ ምንድን ነው?

መልስ:-
ይህ ቢድዓ ነው! ይህ ቢድዓ ነው! በነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ ሰለዋት ማውረድ የተደነገገና ጥሩ ነው ነገርግን በቁጥር መገደቡና ወደ እዚህ ወደዚህ (ቦታ) ላክ (መባሉ) ይቢድዓ ነው በርሱ ላይ ምንም መረጃ የለውም።

ይህ ነገር በኛም ዘንድ በሰፊው የተሰራጨ ነው እሄን ያክል ሱብሐሏህ ያለ እሄን ያክል አጅር አለው ለምሳሌ ለ20 ወይም ለ30 ሰው ካስተላለፍክ እሄን ያክል አጅር ታገኛለህ የሚሉ ፅሁፎች ብዙ ናቸው። አንዳንዶቹ በየግሩፑ ሁሉ የተባለው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ በኢዋህነት ሸር የሚያደርጉ አሉ።

ስለዚህ በንዲህ ያለ ጉዳይ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል በዲን ጉዳይ የሚተላለፉ ነገሮችን እንደሰማን ወይንም እንዳነበብን ከመቀበላችን አልያም ከመተግበራችን በፊት ትክክለኛ የቁርኣንና ሐዲሥ መረጃ አለው የለውም የሚለውን ቀድመን ልናጣራና ልናረጋግጥ ይገባናል።

የሸይኹን ንግግር በዚህ ገብተው ያዳምጡ
http://cdn.top4top.co/m_15cf120.mp4

Https://t.me/Daru_Sunnah