Get Mystery Box with random crypto!

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በተለያዩ የሀገራችን ፊልሞች ላይ በድን | DANI SITE

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በተለያዩ የሀገራችን ፊልሞች ላይ በድንቅ ብቃት በመተወን በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደደው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን በህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ለማረጋገጥ መቻሉን አሳውቋል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ፦
- ወጣት በ97፣
- ወንድሜ ያዕቆብ፣
- ላውንድሪ ቦይ፣
- ማርትሬዛ፣
- ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣
- ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣
-  አንድ ሁለት ፣
- ብር ርርር፣
- ወደው አይሰርቁ፣
- ወፌ ቆመች፣
-  እንደ ቀልድ ፣
- ወቶ አደር ፣
- አባት ሀገር
- የሞግዚቷ ልጆች፣
- ይዋጣልን ፣
- ዋሻው፣
- ወሬ ነጋሪ እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።

በጣም  በጣም አዝነናል ለመላው ወዳጆቹ መፅናናትን እንመኛለን