Get Mystery Box with random crypto!

አንዴ እናቴ የተቀቀደደ ልብስ ለመስፋት ፈልጋ በመርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ፡፡እኔም በመ | ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል

አንዴ እናቴ የተቀቀደደ ልብስ ለመስፋት ፈልጋ በመርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ፡፡እኔም በመስጂድ አንዱ ዳዒ ሲናገር የሰማሁት ዳዕዋ ትዝ አለኝ፦"እናቶቻቹህ ክር በመርፌ እንድታስገቡላቸው ሲያዟቹህ ቶሎ አታስገቡት፡፡ማስገባት እንዳስቸገራቹህም አስመስሉ፡፡ይህ እነሱ የእርጅና ስሜት እንዳይሰማቸው ያደርጋል"የሚል ነበር ምክሩ፡፡
እኔም በምክሩ መሰረት መታገል ጀመርኩ፡፡የመርፌውን ቀዳዳ እያየሁ አውቄ እስታለሁ፡፡በሁኔታዬ የታከተቸው እናቴም በእስክቢርቶ ጭንቅላቴን መታችኝ፡፡:
"ሞባይል ላይ ፈጠህ አትዋል እያልኩህ ይኸው ገና በ 20 አመትህ አይንህ ሊጠፋ ደረሰ፡፡"ብላኝም መርፌውን ተቀበለችኝ፡፡

በዕዱሰ-ሷሊሂን

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል