Get Mystery Box with random crypto!

ታላቁ አባት አርበኛ ጋሽ በቀለ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ዳና ሀይኪንግ ወደ ቡልጋ ኢላኒ | Dana Hiking ~ ዳና ሀይኪንግ

ታላቁ አባት አርበኛ ጋሽ በቀለ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

ዳና ሀይኪንግ ወደ ቡልጋ ኢላኒ ጋዝማት የለኝ ገደል ጉዞውን ሲያደርግ ከአካባቢው መልክአ-ምድር ባሻገር ከ ፊታውራሪ ቁንጬ ስር ሆነው ከታላቁ አርበኛ ራስ አበበ አረጋዊ ጎን ለሀገራችን ሰላም እና ነፃነት የታገሉትን ጋሽ በቀለ በመጠየቅ እንዲሁም የአባት አርበኛ መስዋዕትነታቸውን ባይመጥንም ለክብራቸው ምስጋና በተደጋጋሚ አቅርቧል።

እኒህ አባት ከ 114+ አመት በላይ በህይወት የኖሩ ጀግና ሲሆኑ የሰገሌ ጦርነት በተደረገ በሁለተኛው አመት እንደተወለዱም ይናገራሉ። እኒህ ታላቅ አባት አርበኛ ቡልጋን እንድንናፍቅ ያደረጉን ታላቅ ሰው ነበሩ።

ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለዳና ሀይኪንግ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።

እሁድ ወደ ቡልጋ ልናደርገው የነበረውን ጉዞም በዚህ የተነሳ ለመሰረዝ መገደዳችንን እንገልፃለን።