Get Mystery Box with random crypto!

                         #እውነትና ንጋት በቅድሚያ ሰላም ለውድ የጥበብ ቤተሰብ | Dan Admasu

                         #እውነትና ንጋት

በቅድሚያ ሰላም ለውድ የጥበብ ቤተሰብ ለሆናችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ሰላምና ጤና ይብዛላችሁ እያልኩ ላይለኩሉ (ላዕለኩሉ) በተሰኘው በ2012 ሀገርኛ ይዘት ያለው ነጠላ ዜማ ሙዚቃውን ሰምታችሁት ብሎም ወዳችሁት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሽልማት ፕሬግራም ላይ ለመረጣችሁን የጥበብ ወዳጆችና አወዳዳሪ ዳኞች የተሰማኝን ልባዊ አክብሮቴን ለምግለጽ እወዳለሁ፡፡
በመቀጠልም በዚህ ላይለኩሉ (ላዕለኩሉ) በተሰኘው ስራ እንደተለመደው ድንቅ የሙዚቃ አሻራውን ለአተመበት ለድንቁና ብርቁ አይተኬው የሙዚቃ አቀናባሪ ዳግማዊ አለሊ እንኳን ደስ አለህ እንኳን ደስ አለን በማለት የፈጠረብኝ ደስታ ወደር የለውም ለመሸለም እንደማትሰራ ባወቅም ከዚህም በኋላ ግን ብዙ ሽልማቶች በርህ ድረስ መተው እንደሚያንኳኩ ጥርጥር የለኝም፡፡
ከዚህ በመቀጠል ከላይ በርእሴ ወደገለጽኩት ሀሳብ ግን እውነትና ንጋት እያደረ ይጠራል እንዲሉ አበው በማስከተል በውድድሩ ላይ የተሰማኝን ትዝብት ላካፍላችሁ ፡፡
በመጀመሪያ ከትዝብቴ በፊት እንደመጀመሪያ ዝግጅት ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያዘጋጀው ፕሮግራም የጥበብ ሙያተኛውን የሚያነቃቃ መሆኑን መስክሬ ወደ ዋናው ነጥቤ ልመለስ፡፡
ሀምሌ 12/2013 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህልና ቱሪዝም  ለመጀመሪያ ጊዜ ባከናወነው የሽልማት ስነ ስርእት ላይ በሙዚቃ (በቅንብር) ላይለኩሉ (ላዕለኩሉ) የተሰኘው ሙዚቃ ታጭቶ የነበረውና የአወዳዳሪ ደኞችም በቅንብር አሸናፊ ያደረጉት ወይም የመረጡት ዳግማዊ አሊን ቢሆንም በእለቱ በተፈጠረው የአዘጋጆች ወይም የፕሮግራም አቅራቢዎች ችግር እንበለው ወይም በሌላ ባይታወቅም በተፈጠረው ስህተት ግልፅ ባልሆነ መንገድ ሽልማቱን በማዛባት ለሌላ እንዲሰጥ ሆኖ ነበር እዚህ ጋር ግልጽ  እንዲሆን የጥበብ ሙያተኛው ወይም አርቲስቱ የሽልማቱ  መዳረሻው  የህዝብ ልብና ፍቅር ሲሆን እኛም በዚህ ክብር ሙያ ውስጥ ያለነው የትኛውም የሙያ አጋራችን ቢያሸንፍ እንደኔ የሚከፋው አለብዬ አላምንም ምክንያቱም አንድ የጥበብ ሙያተኛ ሲያሸንፍ አሸናፊዋ ጥበብ ናትና በዚህ ምንም አይነት ግርታ በእናንተ ለምናከብራችሁ የጥብብ ወዳጅና አድናቂ ቤተሰቦች አስረግጨ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
ግን ደግሞ ለህዝብ በሚተላለፍ ሚዲያ ላይ ቲቪም ይሁን ራዲዮ ማለቴ ነው ህዝብ እያየና እየሰማ ተገቢውን እውቅና አሸናፊ ነው ላሉት አካል በህዝብ እውቅናን መንፈግ ስህተት መሆኑን ለማስገንዘብ ነው፡፡
ሞራልንም የሚጎዳ ተግባር ነውና ይህ ስህተት ነገ በሌሎች ተወዳዳሪ እህት ወንድሞች ላይ እንዳይደገም ለማለትና እንድንማማርበት በሚል ነው ብዕሬን ያነሳሁት፡፡
የታናሽም ምክርም ቢሆን ያው ብልህ ከታናሹ ይማራል ነውና እዚህ ላይ ሳላሰምር የማላልፈው ባህል ሚኒስቴር ስህተቱን በማመን በውድድሩ ያሸነፈው ዳግናዊ አሊን የሚኒስቴሩ ቢሮ ድረስ በመጥራት ከታላቅ አክብሮት ጋር የቢሮው አባላት በተገኙበት አርቲስቱን በሚመጥን ዝግጅት ተገቢውን ሽልማት ማለትም አንደኛ የወጣበትን ሰርተፍኬትና የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም የ100,000 ብር ሽልማትን አበርክተውለታል በዚህም ጥፋትን አምኖ ይቅርታ ማለት ወይም  መጠየቅ አዲስ ጅማሮ ነውና በርቱበት እላለሁ፡፡
በመጨረሻም በሃገርው ውስጥም ሆነ በመላው አለም  በምትገኙ ውድ ተከታዮቻችንና  አክባሪዎቻችን ሙዚቃው እናንተ ጋር ያለመድረሱ ምክንያት በመጀመሪያ በሀገር ውስጥ ብቻ እንዲወጣ ውል በመደረጉ ሲሆን ለዚህም አሜሪካ፣ አውሮፓ እንዲሁም በአረብ ሀገራት የነበረውን የሙዚቃውን የመስማት ጥያቄ ባለመመለሳችን ይቅርታ እየጠየቅን በቅርቡ ሁሉንም ዝግጅት ጨርሰን ላይለኩሉ በምስል (በvideo) ይዘን ለመምጣት ዝግጅታችንን ጨርሰናል እስካሁን ላሳያችሁን ትእግስት አክብሮት ግን ያለኝን ክብር ከወገቤ ጎንበስ ከአንገቴ ቀለስ በማለት ዝቅብዬ ለእናንተ ለውድ የሀገሬ ልጆች ለኢትዮጵያዊያን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
ፈጣሪ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ሰላሙንና ምህረቱን ያምጣላት አንድ ያድርገን፡፡

https://bit.ly/3ckOkCF
ዳን አድማሱ የዩቲዩብ ቻናል ሊንኩን በመጫን  ቤተሰብ ይሁኑ።

ሰላም ለ ኢትዮጵያ
ሰላም ለሰው ልጆች በሙሉ
አንድኢትዮጵያ
#ዳን_አድማሱ