Get Mystery Box with random crypto!

አለሜ ነሽ ክፍል 9 መኪናው ሲገለበጥ ግማሾቻችን ደነዝዘን ግማሾቻችን ጮክን ሌሎቻችን ደ | 🤴Nahi👸Marsi

አለሜ ነሽ

ክፍል 9


መኪናው ሲገለበጥ ግማሾቻችን ደነዝዘን ግማሾቻችን ጮክን
ሌሎቻችን ደሞ ለማምለጥ በመስኮት ሞከርን ግን አልሆነም
መኪናው ተገልብጦ ሁላችንንም ጣር እና ስቃይ ላይ ሆንን በጣም
ተስቃየን አንዱ ጓደኛችን በትንሽ ማቃሰት በኋላ ህይወቱ አለፈ
ከዛም በተራ በተራ ቀስ በቀስ የጣር ድምፅ ጠፋ ካንደኛው
ጓደኛዬ በስተቀር። ከዛም ከብዙ ስቃይ በኋላ የነብስ አድን
ሰራተኞች መጥተው ወደ ጣሬዛ እያርጉ በመኪና ይዘውን ሄዱ
ኡፍፍፍፍፍፍ ስቃይ ውስጥ ሆኔ ከጓደኞቼ ጋር ያሳለፍኩትን
እያስብኩ አዘንኩኝ በጣም እወዳቸው ነበር ልክ እንደ ነብሴ ከ
ነብሴ እኩል ብወዳቸውም የራሴን ነብስ እንጂ የእነሱን ማትርፍ
አልቻልኩም ለነገሩ የኔንም ነብስ ፈጣሪ በጥበብ ነው ያተርፍው
የአንደኛው ጓደኛዬን ጭምር አጋጣሚ እኛ ሁለታችን ከ ጋቢናው እና
ከኋላኛው ወንበሮች መሀል ያለው ወንበር ላይ ነበር የተቀመጥነው
መሀለኛው ቦታ ብዙ አልተጎዳም አለ አዳም ባዘነ ድምፅ ዲና
እየሰማች ሳታስበው ማልቀስ ጀመርች አልቻለችም አዳምም
አብሯት አለቀሰ አዳም እንባውን ጠርጎ ወደ ወሬው ተመለስ
እምምም እና ከዛ እኔ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ብቻ የሆነ ጊዜ
ላይ ካለሁበት ድንዛዜ ስነቃ ሆስፒታል ነኝ ሳሚን አየውት ሳሚ
ማለት መዝናናት የሚባል ነበር በጭራሽ የማይወድ እና ከራሱ
ጋር ጊዜ የሚያሳልፍ ሰው ነው በእዛ ምክንያት እኛ ለመዝናናት
ስንሄድ እሱ አልመጣም ነበር የሚለን ሁሌም እንዲህ አይነት
ነገሮች ላይ አይሳተፍም ሳሚን ሳየው ፈገግ አልኩኝ እሱም ፈጠን
ብሎ እ አንዴት ነክ ብሎ ረጋ ባለ መልኩ ጠየቀኝ እኔም በፊቴ
ደህንነቴን ገለፅኩለት ነርስ ጠርቶ እስኪመጣ እርፍት እንዳደርግ
እና አንድ ጓደኛው ከሻይ ቤት ቡና ልታመጣ እንደሄደች እና
እንደምትመጣ ነገረኝ ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ እሺ አልኩት ከዛም ሄደ
እንደሄደ በእጇ 2 ሻይ ይዛ መጣች ሳያት በጣም ደነገጥኩኝ
በጣም ልቤ ሲመታ ክፍሉን ያናወጠው መሰለኝ የፈጣሪ ያለ
እንዴት መጣች ብዬ ገረረመኝ ሄዋን ነበርች ደስስስ አለኝ ስታየኝ
ሞቅ ደመቅ ባለ ደምፅ እንዴዴዴዴ አዲዬ ፍቅር ነቃክ ብላ ጭምቅ
አድርጋ አቅፋኝ ማውራት ጀመረች የድምጿ ጩሀት እና
የተጫነችኝ ቁስሌን መቆጣጠር እስኪሳነኝ አቅፍኝ ስማኝ አዲዬ
አስደነገጥከን እኮ የኔን ውድ እያለች ትጨምቀኝ ጀመር ቢያመኝም
ህመሜን ዋጥ አደርኩት ምክንያቱም ስታቅፍኝ ካመመኝ ይልቅ
ስላቀፈችኝ ብቻ ደስታዬ በጣምም ትልቅ ስለነበር ከዛም ሁለቱን
አይኔን ግንባሬን ሁለት ጉንጮቼን እና አገጬን አንገቴን ያለ ፋታ
እያፈራርቀች ሳመችኝ ደስታዬ ወደር አልነበርውም የቁስሌም
ህመም በጣም አየለብኝ እእእእ ይቅርታ ግን ቁስሌን ስላት ኣ
ይቅርታ በጣም ስለተደስትኩኝ አላስተዋልኩም የሆነ ነገር ልንገርክ
አለችኝ እሺ አልኳት በጉጉት አፍ አፍፏን ማየት ጀመርኩኝ ቀኝ እጄን
ብድግ አድርጋ ልቧ ላይ አደርገችው የልብ ምቷን እጆቼን
አስጠግታ አስዳሰሰችኝ ልብዋ በጣም ይመታል እጄ ከ አካሏ ጋር ሲነካካ ትንፍሽ አጠራት ዲና አስቆመችው እና እሺ እና አንተስ አለችው አዳምም ቀጠለ የኔን ነገርማ ተይው እንደ ውሀ ፈስሼ እንደሻማ ቀለጬ ምንም አላልኩም ከዛ እሷ
በድጋሚ አይኔን ትኩር ብላ አየችው አየዋት የሆነ ነገር በለኝ
እንጂ አለችኝ ምን ልበልሽ አልኳት በፍቅር አይን አያየዋት አዲዬ
አፍቅርካለው ካላንተ መኖር አልችልም እያልኩክ እኮ ነው አለች
እንባ እየተናነቃት እየተናነቃት መጣና ማልቀስ ጀመርች
በጣም ደነገጥኩ እና በድንጋጤ ብድግ ብዬ እንባዋን ጠርኩላት
አቀፍኳት ለምን ታለቅሻለሽ አልኳት እንባዋን በእጄ እያበስኩ በጣም ደስስስ
ብሎኝ አለችኝ እኔም በምኑ ስላት እንደማፍቅርክ ስነግርክ አይንክ ውስጥ አንደምታፈቅረኝ ስላየው አላስቻለኝም እውነተኛ ግን ያልጠበኩት መልስ ስለሆነ በድጋሚ ደነገጥኩኝ ምንም ቃል ካፌ ሊወጣልኝ አልቻለም በውጤ ግን ለካ
ፍቅር እንዲ ነው? አልኩኝ ከዛም ህመሜ ተነሳብኝ አአ አ አአ ስል
ድንግጥ ብላ ምነው ምን ሆንክ ስትለኝ አይ ምንም ትንሽ አመመኝ
አልኳት እሺ እርፍት አድርግ በላኝ አመቻችታኝ ተኛው ግን እንቅልፍ
አልወሰደኝም ከዛ ትንሽ ቆይቼ እእ ስል ከወንበሯ ብድግ ብላ
ምነው አለችኝ አፍቅርሻለው ያላንቺ መኖር አልችልም እንዳትተይኝ
ልልላት አሰብኩና ፈራው አይ ተይው ምንም አልኳት ልቤ ግን ያለ
ማቋርጥ ይመታል ደስስስ እያለኝ መጣ ከዛ ስናወራ ሰው የሰማን ይመስልሻለል አልኳት እኔጃ ግን ለምን ጠየከኝ ስትለኝ አይ ምን አልባት ስላት ፊቷን አኮሰታትራ እ
መልስልኛ ምን ልትለኝ ነው ሰው ከሰማስ ምን ይሁን እ ንገርኛ
አለች እየጮከች ድምጿ እንኳን ጮሃበት እንዲሁም በጣም ጮክ
ያለ ስለሆነ ሽምቅቅ ድንግጥ አልኩኝ ክትክት ብላ መሳቅ ጀመርች
ግራ ገብቶኝ አፍጥጬ ዝም ብዬ አያት ጀመር ሳቋን ገታ አድርጋ
አትደንግጥ የጮኩብክ ላስደነግጥክ ነው ደሞ ተሳክቶልኛል
አይደል አለችኝ እኔም ቁስሌን በማይጎዳ መልኩ ስቄ በጣም
ጓበዝ ነሽ አልኮት አይዞክ አትደንግጥብኝ የኔ ፍቅር ጓደኛክ ደሞ
ነገ ነው የሚመጣው ቅድም ቡናውን ይዤ ወደክፍል ስመጣ
አግኝቼው እንዳይመጣ እና እኔ ካንተ ጋር ብቻዬን መሆን
ስለምፈለግ እንዳይመጣ ነግሬዋለው ሀኪሞቹም ካላመመክ
አይመጡም ማለቴ ካልጠራናቸው ጠዋት ነው የሚመጡት
አለችኝና በል አሁን ተኛ ብላ አደላድላ በድጋሜ አስተኛችኝ
ግንባሬን ሳመችኝና ወንበሯ ላይ ልትቀመጥ ስትል እጇኝ ያዝ
አረኳትና አጠገቤ ሁኚ አልኳት ት አላርም ቅጠሪና ዶክተሮች
ሳይመጡ ትነሻለሽ አልኳት ፈገግ እያለች እሺ ብላኝ ለሊቱን ሙሉ
ተቃቅፍን ተኛን ከሚያፍቅሩት ከሚወዱት ጋር መሆን እንዴት ደስስስ
ይላል ። አላርሙ ጩኸ አልስማነውም ነበር ጠዋት ዶክተሩ
ሊያየኝ ከ ነርሷቹ ጋር ሲመጣ አየን ሁሉም በስሱ ፍገግ ብለው
ቁልቁል ሲያዩን ጀመር አይኔን ስገልጥ እና ሳያቸው ደነገጥኩኝ
ሄዋንም ተነሳች ግን እሷ ምንም አልመስላትም ደና አደራቹ ብላ
ዘብነን ብላ ጉንጮቼን ስማኝ እርቦኛል ቁርስ በልቼ እመጣለው
ውዴ ብላኝ ወጣች ብሎ አዳም ንግግሩን ገታ። ዲና አዳምን
ኮስተር ብላ እያየችው እንዴ ቀጥልልኛ አለችው ብዙ አስወራሽኝ
የቀር ረው ለነገ ይሁንልሽ ነገስ ማን አለው አላት እሺ አለችው ዛሬ
አላስጨነቀችውም ሄዋን ክፍል ተያይዘው ገቡ። ሄዋን ጣራ ላይ
አይኗን ልክ የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ስው ተክለዋለች አተኩሮም
ሆነ ሳያተኩር ላያት አንድ በጣም ትንሽ ነገር ጠፍታት ወዴትም
እንዳትሄድ ጠብቂያት የተባለች ትመስላለች አዳም እና ዲናን
አላየቻቸውም በመጨርሻ ዲና እህም እህም ብላ ከተመስጦዋ
አነቃቻት ሄዋንም ሁለቱንም እያፈራርቀች አየቻቸው ከዛም አዳም
ላይ አይኖን ጥላ ቀርች አፈጠጠች አስተያየቷ የፍቅር ነው ልክ
ከአደጋው በፊት እንደምታየው አስተያየት አዳም እንባው በአይኖቹ
ሊወጡ ክፉኛ ታገሉት ታገሉት ከዛም አዳም ክፍሉን በፍጥነት ጥሎ ወጣ ሄዋንም በደከመ ድምፅ እናንተ ማናቹ አለቻቸው ዲና ምን እንደምትል ጠፍባት
ተርበተበተች ከዛ...
✎ ክፍል 10 ከ 20 Vote በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
@chel1905
@couple_goal2 ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄