Get Mystery Box with random crypto!

ነገ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳሉ በነገው እለት በተለያዩ የኦሮሚ | Addis Merkato

ነገ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳሉ

በነገው እለት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የዶክተር ዐቢይ መንግስትን የሚደግፍ እና ኦነግ ሼነን የሚቃወሙ ሰልፎች እንደሚካሄዱ ተገለጸ፡፡ ሰልፉ አሁን በመንግስት እየተካሄዱ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እና አጠቃላይ የለውጥ እርምጃዎችን የሚደግፉ የድጋፍ እንዲሁም ፀረ ሰላም ቡድኖችን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ሰልፉ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች የአሰላ ከተማ አንዱ ሲሆን፣ በሰልፉ ላይ በዞኑ ከሚገኙ 28 ወረዳዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል። የድጋፍ ሰልፉ ከህዝብ የመጣ ጥያቄ እንደሆነ የተነገረለት ሲሆን፣ ከ100 ሺህ በላይ የሚሆን ተሳታፊ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአሰላ ከተማ አስተዳደር መረጃ ያመለክታል።