Get Mystery Box with random crypto!

በግንባታ ላይ የነበረው የካርል አደባባይ ለትራፊክ ክፍት ሆነ - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች | Construction Proxy

በግንባታ ላይ የነበረው የካርል አደባባይ ለትራፊክ ክፍት ሆነ

- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በካርል አደባባይ አካባቢ የሚታየውን የትራፊክ ፍስት የተቀላጠፈ ለማድረግ አደባባዩን የማንሳትና በትራፊክ መብራት የመተካት ሥራ ለማከናወን ካለፈው ቅዳሜ ምሽት ጀምሮ የመንገድ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል።

አሁን ላይ የአደባባይ ማንሳትና አስፋልት የማልበስ ሥራ ተገባዶ መንገዱ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በኩል የሚከናወነውን የትራፊክ መብራት ተከላ ሥራን ጨምሮ ሌሎች ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራዎች በአካባቢው በትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ በማያሳድር መልኩ በቀጣዮቹ ቀናት ይከናወናሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች