Get Mystery Box with random crypto!

' የቀድሞ የአቅራቢነት ምዝገባ ከህዳር 30 በኃላ አገልግሎት አይሰጥም ' - የመንግስት ግዥና ንብ | Construction Proxy

" የቀድሞ የአቅራቢነት ምዝገባ ከህዳር 30 በኃላ አገልግሎት አይሰጥም " - የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በመንግስት ግዥ ለሚሳተፉ አቅራቢዎች ባሰራጨው ደብዳቤ የቀድሞው የአቅራቢነት ምዝገባ ከህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም በኋላ አገልግሎት እንደማይሰጥ አሳውቋል።

በዚህም ፤ ከዚህ በፊት በባለስልጣን መ/ቤቱ ድረ-ገጽ (https://www.ppa.gov.et/) ላይ የተመዘገቡ አቅራቢዎች ምዝገባቸው ተቀባይነት የሚኖረው የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓትን (e-GP) መጠቀም ባልጀመሩ ተቋማት ብቻ እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አስገንዝቧል።

በመሆኑም በ https://egp.ppa.gov.et/ ላይ በመግባት ተገቢውን ምዝገባ በማከናወን በመንግስት ግዥ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ አሳውቋ::