Get Mystery Box with random crypto!

እንዴት የሞባይል ባንኪንግ ‘QR’ አገልግሎት ተጠቅመው ገንዘብ መቀበል/ክፍያ መፈፀም ይችላሉ? == | Commercial Bank of Ethiopia - Official

እንዴት የሞባይል ባንኪንግ ‘QR’ አገልግሎት ተጠቅመው ገንዘብ መቀበል/ክፍያ መፈፀም ይችላሉ?
===========

1. ገንዘብ ላኪውና ተቀባዩ አንድ ላይ የማይገኙ ሲሆን

• ገንዘብ ተቀባዩ በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ከሚመጡት አማራጮች ‘ገንዘብ ለመቀበል’ ‘Receive Money’ የሚለውን ይምረጡ፤
• ‘የገንዘብ መጠን እና ምክንያት’ ‘Amount and Reason’ የሚለውን ይምረጡ፤
• የገንዘብ መጠን እና ምክንያቱን አስገብተው ‘ቀጥል’ ‘Continue’ የሚለውን ይጫኑ
• ‘ያጋሩ’ ‘Share’ የሚለውን ይጫኑ፣
• ‘በማስፈንጠሪያ መልክ ያጋሩ’ ‘Share as a link’ የሚለውን ተጭነው ‘እሺ’ ‘Ok’ የሚለውን ይምረጡ፣
• በSMS፣ በቴሌግራም እና በሌሎችም መልእክት መላላኪያ መንገዶች ተጠቅመው ማስፈንጠሪያውን ለገንዘብ ላኪው ይላኩ፣
• ገንዘብ ላኪው በመልእክት የደረሰውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመክፈት የሚላከውን የገንዘብ መጠን እና ምክንያት አረጋግጦ ገንዘብ ማስተላለፍ/ክፍያ መፈፀም ይችላል፡፡

2. ገንዘብ ላኪውና ተቀባዩ በተመሳሳይ ቦታ የሚገኙ ከሆነ

• ገንዘብ ተቀባዩ በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ከሚመጡት አማራጮች ‘ገንዘብ ለመቀበል’ ‘Receive Money’ የሚለውን ይምረጡ፤
• የገንዘብ መጠን እና ምክንያቱን አስገብተው ‘ቀጥል’ ‘Continue’ የሚለውን ይጫኑ
• ገንዘብ ላኪው በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ከሚመጡት አማራጮች ‘ስካን ኪው አር’ ‘Scan QR’ የሚለውን ይምረጡ፤
• የሚላከውን የገንዘብ መጠን እና ምክንያት በማስገባት ገንዘብ በቀላሉ መላክ/ክፍያ መፈፀም ይቻላል፡፡