Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለ | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95.4 በመቶ የሚሆነውን ማስመለስ ቻለ፡፡
**********************
ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801,417,747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር የተገለጸ ሲሆን ከዚህም ገንዘብ ብር 764,567,820 ማስመለስ ተችሏል፡፡ ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95.4 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 4.6 በመቶ ብር 36,848,584 ገንዘቡን ተመላሽ ካላደረጉት ግለሰቦች የማስመለስ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡