Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም አቀፍ የደም ለጋሾች ቀን #WorldBloodDonorDay ===================== | Commercial Bank of Ethiopia - Official

ዓለም አቀፍ የደም ለጋሾች ቀን
#WorldBloodDonorDay
=========================
በዓለም የጤና ድርጅት መስራችነት እ.ኤ.አ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ ጁን 14 (ሰኔ 7) የሚከበረው ዓለም አቀፍ የደም ለጋሾች ቀን፦
• የደም ልገሳ አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ መፍጠር፣
• ደም ለጋሾች በአንድ ሀገር የጤና ስርዓት ላይ ለሚያበረክቱት ምትክ የለሽ አስተዋጽኦ እውቅና መስጠት እና
• ብሄራዊ የደም አቅርቦት አገልግሎት ሰጪዎች እና ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያከናውኗቸውን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረቱ የደም ልገሳ መርሃ ግብሮች እንዲጠናከሩና እንዲስፋፉ በሀገር አቀፋዊና አካባቢያዊ ዘመቻዎች ማገዝን ዋነኛ ዓላማ በማድረግ ይከበራል ፡፡

ደም እና የደም ውጤቶች በተለያዩ የጤና እክሎች፣ አደጋዎች፣ በህክምና ጊዜ በሚፈጠሩ አጋጣሚዎች የደም መፍሰስና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ለሚገጥማቸው ታካሚዎች እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ዓለም ላይ በደም ፍላጎትና አቅርቦት ላይ ያለመመጣጠን ችግር የሚስተዋል ሲሆን፣ ይህም በተለይ የደም አቅርቦት ፍላጎቶች በብዛት በሚከሰትባቸው ህፃናትና ሴቶች ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽእኖ ከባድ ነው፡፡

ቀላል ነገር ግን የከበረ ተግባር የሆነውን በፈቃደኝነትና በመደበኛነት ደም የመለገስ ተግባር ሁሉም በመፈጸም ማህበረሰቡን ማጠናከር፣ የጤና ስርዓቱን ማገዝ ብሎም ህይወትን ማትረፍ ይቻላል፡፡

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የደም ለጋሾች ቀን ‘ደም መለገስ የአብሮነት መገለጫ ነው፤ ተባብረን ህይወት እናድን’፣ ‘Donating blood is an act of solidarity. Join the effort and save lives’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከብሄራዊ የደም ባንክ ጋር በመተባበር በተለያዩ ጊዜያት የሠራተኞች የደም ልገሳ ፕሮግራሞችን በማካሄድ በሀገራችን ከደም እጥረት ጋር ተያይዞ በጤና ስርዓቱ ላይ ክፍተት እነዳይፈጠር በሚያደርገው አስተዋጽኦ ይታወቃል፡፡